Logo
EBC
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት አስተላለፉ
********************

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ለ25 ዓመታት በማገልገል የብር ኢዮቤልዩአቸውን እያከበሩ ላሉት የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ናሬንድራ ሞዲ እአአ ከ2001 እስከ 2014 የጉጃራት ግዛት ዋና አስተዳዳሪ፣ ከዚያ ወዲህ ደግሞ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው፣ የኢትዮጵያ እና የሕንድ አጋርነት ባለፉት ዓመታት ይበልጥ እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን ሕንድ የሰጠቻትን ድጋፍ እንዲሁም ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት በማሳያነት ጠቅሰዋል።

አያይዘውም፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ አጋርነት ይበልጥ ለማሳደግ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
#ትልቅ_ሀገር ! #ትልቅ_ሕዝብ ! #ታላቅ_ርዕይ !
#ethiopia #india #bilateral #partnership #abiyahmed #narendramodi #ebc

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.