Logo
AHADU RADIO FM 94.3
ዜጎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ጉዳት እንዳይደርስባቸው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ መሪነት በሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ጥምረት እ.ኤ.አ ከ2022 አንስቶ የሰላም እጦትና የተፈጥሮ አደጋ በነበረባቸው አካባቢዎች ሲተገበር የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማብቃቱን አስታወቀ።

ጥምረቱ ከ40 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ የቆየ ሲሆን ባለፉት አራት አመታት ሲተገብር የቆየው “ጂኦፕ 2” የተሰኘው ፕሮጀክት ተጠናቆ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

በካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ዘመዴ ዘውዴ ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው ፕሮጀክት የተወሰዱ ትምህርቶች በቀጣይ ለሚተገበረው ፕሮጀክት ግብዓት ይሆናል።

ካለፈው አንድ አመት ወዲህ የውጭ ድጋፎች መቀነስ እንዲሁም የሀብትና የተረጂዎች ቁጥር አለመመጣጠን ትልቅ ፈተና እንደነበር ገልፀው ሆኖም ግን ሁሉንም የእርዳታና መልሶ ማቋቋም ስራዎች ሰርተናል ብለዋል።

በቀጣይ ተፈናቃዮችን እና በገጠር የሚገኙ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በልዩ ሁኔታ የመደገፍ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በአየር ሁኔታ ለውጥ ምክንያት የሰብል ምርት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ እና ጉዳት በሚያጋጥምበት ወቅት ዜጎችን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በቀጣይ የሚሰሩ የእርዳታ ስራዎች ከመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካላት ብቻ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

በመሰረት ሙሉ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.