በዉቅሮ ዙሪያ የከባድ መሣሪያ እየተሰማ ይገኛል!
በዉቅሮ ዙሪያ የከባድ መሣሪያ እየተሰማ እንደሚገኝ አንድ የከተማው ነዋሪ ለዶቸ ቬለ ተናገሩ። የትግራይ የሰላም ኃይል አባላት ዉቅሮ መድረሳቸውን የታጣቂ ቡድኑ አንድ አዛዥ እንደተናገሩ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቦ ነበር።
ይሁንና ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪ ግን ከትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ በ50 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው ዉቅሮ “በአሁኗ ሰዓት ከሁሉም ውጪ ናት” ሲሉ አስረድተዋል። እስከ ትላንት ማታ ድረስ በከተማው የትግራይ ኃይሎች አባላት እንደነበሩ የገለጹት የዉቅሮ ነዋሪ በአዲግራት እና ሐውዜን አቅጣጫዎች መውጣታቸውን ገልጸዋል።
ነዋሪው “ስለ ኤርትራ ጦር በዉቅሮ አካባቢ የታየ ክስተት የለም” ሲሉ ተናግረዋል።ዶቸ ቬለ በአካባቢው ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በገለልተኝነት ማረጋገጥ አልቻለም።
ከመቐለ ወደ አዲግራት የሚያልፉ መንገደኞች የመከላከያ ሠራዊት “እየመጣ ነው የሚል መረጃ” ለከተማው ነዋሪዎች በመናገራቸው “ሰዉ ራሱን እየጠበቀ” ይገኛል።
እሁድ እና ሰኞ በዉቅሮ “የተለያዩ [የዘረፋ]ሙከራዎች ስለነበሩ እሱን ለመከላከል በቡድን አካባቢውን እየጠበቀ” እንደሆነ አስረድተዋል። የከተማው ነዋሪዎች “ተባራሪ ጥይት እንዳይመጣ ተኩስ እንዳይከፈት ሥጋት” እንዳላቸው ከዉቅሮ በስልክ ያስረዱት እማኝ “እስካሁን ግን ከከባድ መሳሪያ ድምጽ ውጪ” የተሰማ አለመኖሩን ገልጸዋል።በከተማው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ባይቋረጡም ኤሌክትሪክ አለመኖሩን የዉቅሮው ነዋሪ ገልጸዋል።
Via DW
@YeneTube FikerAssefa

1 day ago