የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጦርነትን ለማስቆም የሚደረጉ ድርድሮችን ውድቅ አደረጉ
ጄነራሉ ሁሉንም ግዛት ከRSF መልሰው እንደሚቆጣጠሩም ቃል ገብተዋል
ማክሰኞ እለት ተባብሶ በቀጠለው ግጭት የምዕራብ ኮርዶፋን ግዛት ቢያንስ 10 ሰላማዊ ሰዎች የተገደሉበት ሲሆን በብሉ ናይል ግዛት ደግሞ 5,500 ሰዎች ተፈናቅለዋል።
አል-ቡርሃን በከፊል በወታደራዊው ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል (RSF) ቁጥጥር ስር ያሉትን እያንዳንዱን መሬት መልሰው እንደሚቆጣጠሩ ቃል ገብተዋል። እንዲሁም የሶስት ዓመት ተኩል ጦርነትን ለማስቆም የሚደረጉ ድርድሮችን ውድቅ ማድረጋቸው ነው የተሰማው።
እንዲሁም ማክሰኞ ዕለት በሰሜን ሱዳን መሮዌ አካባቢ በሚገኘው ቪሌጅ 5 በተባለ ቦታ በተደረገ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል ሲል የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የሱዳን ሠራዊት እና የRSF አዛዦች ከፊል ወታደራዊው ኃይል ከሱዳን ሠራዊት ጋር ሊዋሃድበት በነበረው እቅድ ዙሪያ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ እ.ኤ.አ ከ2023 ጀምሮ ሲዋጉ ቆይተዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በአለም አቀፍ ተቋማት ግምት መሰረት ይህ ግጭት አስር ሺዎችን የገደለ ሲሆን 13 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አፈናቅሏል።አል-ቡርሃን ጦርነቱን መቀጠላቸውን ባስታወቁበት ወቅት በአካባቢው የበጎ አድራጎት ድርጅት እንደተገለጸው በሱዳን ምዕራብ ኮርዶፋን ግዛት በ RSF ጥቃት 10 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል። በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።
የዳር ሃማር ድንገተኛ አደጋ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ RSF በኤን ናሁድ ምስራቃዊ ገጠራማ አካባቢዎች በሚገኘው አቡ አጃል መንደር ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተለያዩ ጥሰቶችን ፈጽሟል ሲል ከሰዋል።የሱዳን ሠራዊት በአቅራቢያው ወደምትገኘው ሰሜን ኮርዶፋን ግዛት ውስጥ ድሎችን ካስመዘገበ በኋላ RSF በምዕራብ ኮርዶፋን ኃይሉን እየሰበሰበ ይገኛል።
በሌላ በኩል በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት፣ የጸጥታውን ሁኔታ መባባስ ተከትሎ ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ ከ5,500 በላይ ሰዎች ከመንደሮቻቸው መፈናቀላቸውን አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ማክሰኞ ዕለት አስታውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ የሱዳን አካላት ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረጉ ንግግሮች ላይ መሪነቱን መውሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የአሜሪካ የዓረብ እና አፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ ሰኞ ዕለት በኤክስ ገጻቸው ላይ በሰጡት አስተያየት ሰላም ሊመጣ የሚችለው በሱዳናውያን ባለቤትነት እና መሪነት በሚካሄድ አጠቃላይ ብሔራዊ ውይይት እና ወደ ሰላማዊ መንግስት በሚደረግ ሽግግር ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ወር እንደገለጸው የሱዳን ሠራዊት ኃይሎችም ሆኑ RSF እንዲሁም የሁለቱ ወገኖች መሪዎች «ለሱዳን ህጋዊ እና ህገ-መንግስታዊ አስተዳደር ውክልና አይሰጡም»።
በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል Photo

2 days ago