በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ የመኖሪያ ቤት ምግብ ሽያጮች ላይ የጤና ስጋት ጥቆማ ከደረሰ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች አማካይነት የኦንላይን የምግብ ማዘዣዎችን በመቀበል፣ በግል መኖሪያ ቤቶችና በድብቅ ቦታዎች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የምግብ ምርቶች ላይ የጤናና የደህንነት ስጋት መኖሩ ከተጠቆመ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአሐዱ አስታውቋል።
ተቋሙ የብቃት ማረጋገጫ (ሰርተፊኬት) ሰጥቶ እውቅና ከሰጣቸው ህጋዊ የምግብና የጤና ተቋማት ውጭ በኦንላይንና በመኖሪያ ቤቶች ደረጃ በድብቅ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተቋሙ አስቀድሞ የማወቅና የመቆጣጠር አሰራር እንደሌለው ለአሐዱ የተናገሩት የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ ብርቄ ናቸው
ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ የቤት ለቤት የምግብ ዝግጅትና ሽያጮች ላይ በህብረተሰቡ በኩል የጥራት፣ የደህንነት ወይም የጤና ስጋት መኖሩን የሚያመላክቱ ጥቆማዎች ከደረሱ፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥቆማውን መሰረት በማድረግ የተገለጹትን ቦታዎች በመፈተሽና በመቆጣጠር አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል።
ማንኛውም የምግብ ዝግጅትና ማቅረብ ስራ ላይ ለመሰማራት የሚፈልግ አካል አስቀድሞ ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመቅረብ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል ብለዋል።
አስፈላጊውን ደረጃ አሟልተው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሳይይዙ ምግብ ማዘጋጀትና ማሰራጨት በራሱ ህገ-ወጥነት በመሆኑ፣ በጥቆማ በሚደረጉ ፍተሻዎች ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ አካላት ላይ ተጠያቂነት እንደሚሰፍን አሳስበዋል።
አክለውም ፤የባለስልጣኑ ባለሞያዎች መስፈርቱን አሟልተው የተመዘገቡ ህጋዊ ተቋማትን በቀጣይነት በዓመት አራት ጊዜና እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው የክትትልና የቁጥጥር ስራ እንደሚያከናውኑባቸው ገልጸዋል።
ህብረተሰቡም በጤናና በምግብ ደህንነት ላይ ስጋት የሚፈጥሩ መሰል ህገ-ወጥ አሰራሮችን ሲታዘብ ጥቆማ በመስጠት መተባበር እንዳለበት ጠቁመዋል።
በወልደሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

2 days ago