Logo
Getu Temesgen
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አዲስ አደረጃጀትና የስያሜ ለውጥ
#ethiopia | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ልዩ ስብሰባው የፌደራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።

በስብሰባው ላይ የመንግሥት ተወካዩ አቶ ፍቃዱ ከተማ እና የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ በረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን፣ የማሻሻያው ዋና ዓላማ የሥራ ክፍሎቹን አደረጃጀት ከተልዕኳቸው ጋር በማጣጣም የተቋማቱን አፈጻጸም ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

በቀረበው ረቂቅ መሠረት የአገሪቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ቁጥር 22 ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን፣ በርካታ የመዋቅርና የስያሜ ማሻሻያዎች ተደርገዋል።

በዚህም መሠረት ቀድሞ የነበሩት የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የቱሪዝም ሚኒስቴር ተቀናጅተው «የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር» በሚል በአዲስ መልክ እንዲደራጁ ተደርጓል።

በተጨማሪም «የፕላንና ልማት ሚኒስቴር» የነበረው ተቋም «የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር» በሚል አዲስ ስያሜ የተካ ሲሆን፣ «የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር» ደግሞ «የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር» ተብሎ እንዲቀየር በረቂቅ አዋጁ ተመላክቷል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.