Logo
AHADU RADIO FM 94.3
በ 2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 65 በመቶ የጤና መድህን ሽፋንን ደግሞ 85 በመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በ 2019 በጀት ዓመት በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አበይት ተግባራ እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የሀገሪቱን የኃይል ተደራሽነት 65 በመቶ ለማድረስ ታቅዷል ብለዋል።

በሌላ በኩል የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሽፋንን ወደ 85 በመቶ ከፍ ለማድረግ ፣ በትምህርት ቤት የተማሪዎች የምገባ ሽፋንን ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃና የደን ሽፋንን አሁን ካለበት 26 በመቶ በላይ ከፍ ለማድረቅ መታቀዱን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ተጠቃሚነትን በስፋት ማዳረስ እንዲሁም የመሶብ አገልግሎት ማዕከላት ቁጥርና አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንዲበራከቱ ማድረግ ሌላው የመንግስት አቅጣጫ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህንን ዕቅድ እውን ለማድረግ መንግስት አዳዲስ አሰራሮችና አደረጃጀቶች እንደሚከተል የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ የዓመቱን ዕቅድ የሚያስፈጽሙ አካላት ዋዛ ፈዛዛ ልምምዶችን በመተው በትጋትና በህዝብ አገልጋይነት ስሜት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በስፍራሽ ደመላሽ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.