Logo
FastMereja
የእንግሊዝ ኤንባሲ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውጥረቱ አሳሳቢ ነው አለ
​ #fastmereja I ​የብሪታንያ (የዩናይትድ ኪንግደም) ኤንባሲ በአዲስ አበባ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ። ኤንባሲው በሰጠው መግለጫ፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አካታች እና ሰላማዊ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲኖራቸው የአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሽምግልና ጥረት ለሚደረገው ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዩናይትድ ኪንግደም ዝግጁ መሆኗን አረጋግጧል።

​በመግለጫው የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት ማስጠበቅ ያለውን ትልቅ ፋይዳ እንደገና አፅንኦት ሰጥቶ የገለጸው ኤንባሲው፤ በተጎዱ አካባቢዎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ እና ህይወት አድን ዕርዳታ ለተቸገሩት እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም ሁሉም አካላት ደህንነቱ የተጠበቀና ያልተገደበ የሰብአዊ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዲፈቅዱ እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁ አሳስቧል።

​በሌላ በኩል፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ባለፉት ጊዜያት እየተባባሰ በመጣው ውጥረት የተሰማውን ጥልቅ ስጋት የገለጸው የብሪታንያ ኤንባሲ፤ በክፍለ አህጉሩ የሚገኙ ሀገራት ሁሉ የጎረቤቶቻቸውን ብሔራዊ ሉዓላዊነትና ግዛት አንድነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።

ኤንባሲው አያይዞም ግጭቶችን ለማቀዝቀዝ፣ በንግግር ለመፍታት እንዲሁም ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉም ተሳታፊ አካላት አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርጉ አበክሮ አሳስቧል።

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.