በእሬቻ በዓል ላይ ስልክ የሰረቁ ግለሰቦች በ4 ዓመት ከ3ወር ና በ2 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት ተቀጡ
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል አከባበርን አጋጣሚ በማድረግ የታዳሚዎችን ስልክ የሰረቁ ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ገልፇል።
የመምሪያው የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ እንደገለጹት ተከሳሽ መሻሩ ከድር መስከረም 22 ቀን ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ የ12 ሺህ ብር ግምት ያለው «ቴክኖ» ሞባይል ስልክ ሲሰርቅ፣
ሁለተኛው ተከሳሽ መለሰ አባቡ ደግሞ መስከረም 24 ቀን በበዓሉ ስፍራ የ20 ሺህ ብር ግምት ያለው «ሳምሰንግ» ሞባይል ሲሰርቅ በበዓሉ ታዳሚዎችና በፖሊስ አባላት ቅንጅት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ፖሊስና በፍትህ አካላት ቅንጅት የተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት የቀረበውን የፖሊስ የምርመራ መዝገብና ማስረጃ መርምሮ በሰጠው ውሳኔ መሻሩ ከድር በ4 ዓመት ከ3 ወር፣ መለሰ አባቡ ደግሞ በ2 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል።
ተዘርፈው የነበሩት ሞባይል ስልኮች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለባለቤቶቻቸው የተመለሱ ሲሆን፣ ተጎጂዎችም በተሰጠው ፈጣን የመፍትሔ እርምጃ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ፖሊስ በተከሳሽ መሻሩ ከድር ላይ ባደረገው ተጨማሪ ምርመራ ሌላ ባለቤት ያልታወቀ «ሳምሰንግ» ስልክ ማግኘቱን አስታውቋል። የስልኩ ባለቤት የሆናችሁ ግለሰብ አስፈላጊውን ማስረጃ በመያዝ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ በአካል በመቅረብ
ንብረታችሁን መረከብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
Via Addis Ababa Police
#ዳጉ_ጆርናል

6 days ago