Logo
AHADU RADIO FM 94.3
10 ሺህ የቡና ሲኒዎች የተሰበሰቡበት ዝግጅት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰፈረ

በኢትዮጵያ የቡና ታሪክና ባህልን ከቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት 10 ሺህ ባህላዊ የቡና ሲኒዎች የተሰባሰቡበት ዝግጅት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ማስፈሩ ተገለጸ።

ምስራቅ አፍሪካ ኢንተርቴመንት ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ መርሃ-ግብር፣ በልዩ ዲዛይን የተገነባ መሆኑ ተጠቅሷል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ እስከዳር ግሩም እንዳስረዱት፣ የቡና ሥነ-ሥርዓት ለሽምግልና እና ለማኅበራዊ ግንኙነቶች የሚያገለግል ባህላዊ እሴት ነው።

ባህሉን በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅ እና የቱሪዝም አበርክቶውን ለማሳደግ በቀጣይ ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚሠሩም ገልጸዋል።

የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሥራ አስኪያጅ አሸናፊ ዓለሙ በበኩላቸው፣ ክንውኑ ሀገራዊ የቡና ከፍታን ከማሳየት ባለፈ ለአፍሪካ የባህልና ቱሪዝም ልማት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

በአበረ ስሜነህ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.