Logo
SeledaPost
በግሸን ደብረ ከርቤ በዓል ላይ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ምዕመናን መታደማቸዉ ተነገረ፡፡

​በትላንትናው ዕለት መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በታሪካዊዋቷ ግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የተከበረው ዓመታዊው የንግሥ በዓል ላይ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት በድምቀት ተከብሮ ዉሏል ።
 
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የተወጣጡ ምዕመናን በዓሉን ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም አክብረው ወደየአካባቢያቸው እየተመለሱ መሆኑን የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መምህር አባ ብስራተ ገብርኤል ክፍለማሪያም ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል ።

ዋና አስተዳዳሪው እንደገለፁት የዘንድሮው የበዓሉ ታዳሚ ቁጥር ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ ያለው ሲሆን ከ2.5 ሚሊዮን በእጅጉ እንደሚበልጥ ገልጸዋል ።

ከበዓሉ አስቀድሞ በበዓሉ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ የትራፊክ መጨናነቅና የመንገድ አደጋ ስጋቶችን ለመቀነስ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስር በሚገኘው የግሸን መገንጠያ የ17 ኪ.ሜ የመንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት የነባር መንገድ ጥገና ሥራዎች መከናወናቸዉ ተገልጿል ።

Seledadotio
Seledadotio
5 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.