Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የተማሪዎች ተቃውሞ ወደ ሁከት በመቀየሩ ምክኒያት በመቶዎች የሚቆጠሩ የፈረንሳይ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

ባለፈው ሳምንት በፓሪስ ውስጥ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ ወደ ፈረንሳይ በመስፋፋቱ እና እየጨመረ በሄደው ሁከት ምክኒያት፣ 400 የሚጠጉ የፈረንሳይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው የቆዩ ሲሆን አሁንም በዕለተ ዓርብ ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

ተማሪዎቹ ተቃውሟቸውን እያሰሙ የሚገኙት የመምህራን እጥረት እና የትምህርት ቤት ህንፃዎች መበላሸትን ጨምሮ በተለያዩ ቅሬታዎች ሳቢያ ነው። መንግስት ግን እንቅስቃሴውን የጀመሩት አስተማሪዎቹ ሳይሆኑ ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ናቸው ሲል ከሷል።

ለጠቅላይ ሚኒስትር ሴባስቲያን ሌኮርኑ ቅርብ የሆኑ አካላት እንደገለጹት፣ ሀሙስ ዕለት በተካሄደው የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቶች የተቃውሞ እንቅስቃሴው የፍራንስ አንቦውድ አባላትን ጨምሮ በፅንፈኛ ፖለቲከኞች አነሳሽነት የተጀመረ መሆኑን ገልጸዋል።

ሰላማዊ ነጋሲ

#ዳጉ_ጆርናል
10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.