ለተከታታይ ሶስት ቀናት የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በባቱ ከተማ አስተዳደር ሙሐዲን አርጆ ቀበሌ ውስጥ በተከታታይ ሶስት ቀናት የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሠብ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታውቋል።
የባቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ ወንጀል መርማሪ ሣጅን ስንታየሑ አሠፋ እንደገለፁት፣ተከሣሽ ጁጊ ጀልዶ ሳፎ የተባለ የአስራ ስምንት አመት ልጅ፣በእነዚህ ቀናት ውስጥ የስርቆት ወንጀል ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ውሎ የሕግ ውሣኔ አግኝቷል።ተከሣሹ፣ግምቱ 99ሺህ ብር የሚያወጣ ብረታ ብረቶችን፣ሽቦዎችን፣ቆርቆሮዎችንና ሌሎች ለግንባታ የሚውሉ ቁሣቁሶችን በሶስት ቀን እየተመላለሰ ሲሰርቆ እንደነበር ገልፀዋል።
ይህ ተከሣሽ ቁሣቁሶቹን ከሠረቀ በሗላ በአንድ ባዶ ቤት ሲያከማች የነበረ ሲሆን በቁጥጥር ስር ሲውልም በርካታ የግንባታ ቁሣቁስ በማስረጃነት መያዙ ተነግሯል።ፖሊስም በተከሣሹ ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ በከባድ ስርቆት ወንጀል ክስ መስርቷል።
ክሱን የተመለከተው የጅዶ ኮቦልቻ አዳሚ ቱሉ ወረዳ ፍርድ ቤት፣መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ጁንጊ ጀልዶ ሣፎ የማይገባውንና የሌላ ግለሠብ ንብረትን በቀጥታ የራሱ ንብረት አድርጎ በመውሰዱ ጥፋተኛ ተብሎ በአምስት አመት እስራት እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑን ሣጅን ስንታየሑ አሠፉ ጨምረው ገልፀዋል።
#ዳጉ_ጆርናል

7 days ago