Logo
AHADU RADIO FM 94.3
በከፍተኛ የምግብ እጥረት ለተጎዱ ሕፃናት የሚውለውን "ፕላምፕሌት" የተሰኘ አልሚ ምግብ በሚሸጡ እና በሚያዘዋውሩ ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ተገለጸ

በሕገ-ወጥ መንገድ ፕላምፕሌት የተሰኘውን አልሚ ምግብ ሲሸጥም ሆነ ሲጠቀም በተገኘ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአሐዱ ሬድዮ እንዳስታወቀው፣ ምርቱ በከፍተኛ ሁኔታ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ሕፃናት በሕክምና ትዕዛዝ ብቻ የሚሰጥ ነው።

የባለሥልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው እንዳስታወቁት፣ ምርቱ እንደ ምግብ የሚቆጠር ሳይሆን በሕክምና ትዕዛዝ የሚሰጥ መድኃኒት ቢሆንም፤ ጡንቻን ለማዳበር እና ለተለያዩ አገልግሎቶች በሕገ-ወጥ መንገድ የሚጠቀሙ ግለሰቦች በመኖራቸው ሕፃናት እየተጎዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ችግሩን ለማስቀረት ከአጋር አካላት ጋር የቁጥጥር ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

ባለፈው ዓመት ብቻ ምርቱን ሲያዘዋውሩ በፖሊስ የተያዙ ግለሰቦች ለእስራት መዳረጋቸውን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

ሕብረተሰቡ የምርቱን ዓላማ ተረድቶ አስፈላጊውን ጥቆማ መስጠት እንዳለበት አቶ እስጢፋኖስ አሳስበዋል።

ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ ያየ ማንኛውም ሰው በነፃ የስልክ መስመር 8864 ጥቆማ እንዲሰጥና በተቆጣጣሪዎች እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል

በስፍራሽ ደመላሽ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
8 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.