🥊 ሆርጌ ሄሱስ Vs ሮናልዶ 🥊
ብዙውን ጊዜ በ ሁለት ሰዎች መሀከል
" አብዝቶ መከበር " የሚፈልግ አይነት ማንነት የሚኖር ከሆነ አብሮ መስራት ፣ መማር ፣ ጓደኝነት መፍጠር ከባድ ሊሆን ይችላል። በ እርግጥ መከበርን የማይፈልግስ ማን አለ? ነገር ግን አንድ ሰው ለረዥም አመታት በነበረው ሞያ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ግዙፍ የስራ ፕሮፋይል ሳይወድ በግዱ ወደዚህ ብዙዎቻችን ወደምንፈልገው መከበር የሚለውን ስሜት ከ ትልቅ ቁጣ ጋር ይዞት ይመጣል። በ እግርኳሱ ደግሞ ይህ ስሜት በ ተጫዋች እና በ አሰልጣኝ መሀከል የሚፈጠር ከሆነ መልበሻ ክፍሉን ከ ቁጥጥር ውጪ የሚያደርገው ይሆናል።
በ 1954 በ ሀገረ ፖርቱጋል ተወልደው በ አማዶራ ከተማ እድገታቸውን ያደረጉትና በ ፖርቱጋል የማሰልጠንም ሆነ በመጫወት የስራ ህይወታቸውን የጀመሩት ሆርጌ ሄሱስ የበለጠ በ አሰልጣኝነት የስራ ህይወታቸው በርካቶቻ ያውቋቸዋል። አንዳንድ ሰዎች ፊታቸውን አይታቹ ገና ምን አይነት ማንነት ሊኖራቸው እንደሚችል ትገምታላቹ በ እርግጥ ቁጡ ፊት ያላቸው ሰዎች ሁሉ ተቆጪ ባይሆኑም። ሆርጌ ሄሱስ ግን የፊት ገፅታቸውን አይታቹ ስለ ሞገዳማ ባህሪያቸው ብትገምቱ አትሳሳቱም።
ከዚህ ቀደም በ ፍላሚንጎ ስኬታማ በነበረ የአሰልጣኝነት ቆይታቸው ወይንም በ ስፖርቲንግ ሊዝበን በቆዮባቸው እንዲሁም በ ቤኔፊካ ባሳለፏቸው ወቅቶች ላይ የነበራቸውን ጋዜጣዊ መግለጫዎች ወይንም ተጫዋቾቻቸውን የሚቆጣጠሩበትን መንገድ የሚያውቅ ሰው ከ ሰሞኑ ከ ሮናልዶ ጋር የገቡበትን እሰጣ ገባ በ ጥቂቱም ቢሆን ሊረዳ ይችላል። ወቅቱ 2016 ላይ ነበር እናም በ ስፖርቲንግ ሊዝበን ቤት በነበሩበት ወቅት ላይ አንድ ጋዜጠኛን በ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰአት ላይ ቅር ተሰኝተውበት በ ቁጣ " ዝም ማለት ትችል ይሆን? " ሲሉ ተናግረውታል ፤ እሱ ብቻ ሳይሆን በቅርብ ጊዜ በ አልናስር አሰልጣኝነቱ ጊዜ ላይ ሳለ አንድ ጋዜጠኛ ከዚህ ቀደምም በ ፖርቶ ሲያሰለጥን ይበልጥ የማሸነፍ ንፃሬ ሲወስደበት በቆየው ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ ቡድን በ አል ኢትሀድ ተሸንፎ በቁጥሮቹ የበላይነት ስለተወሰደበት ይህንን ጥያቄ ሲያነሳለት " ይሄ ደግሞ ምን የሚሉት ጥያቄ ነው? " ሲል በ ቁጣ ተሞልቶ መልሶለት ነበር።
በ አጠቃላይ ሆርጌ ከ ጋዜጠኞች ጋር በ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰአት ላይ ግብግብ ውስጥ የሚገባ ፣ ከ ክለብ ፕሬዚዳንት ወይንም ባለቤት ጋር በቀጥታ ፀብ ውስጥ ለመግባት ቅርብ የሆነ ፣ መልበሻ ክፍል ውስጥ ተጫዋቾቹ ሀሳቡን የሚፃረኑት ከሆነ ቅጣቱ ከበድ የሚል አይነት የአሰልጣኝነት ማንነት አለው። በ አንፃሩ ሮናልዶን በርካቶች ያውቁታል በታሪክ ከታዮ ትልቅ ተጫዋቾች መካከል ብቻ ሳይሆን ትልቅ የሚድያ መስእብ የሆነ እና ካሜራዎች ሁሉ ሌንሶቻቸውን የሚያነጣጥሩበት እሱም ቢሆን መሰማትን አብዝቶ የሚፈልግ እና ከ አሰልጣኞችም ቢሆን ለ በርካታ አመታት በገነባው ትልቅ የእግርኳሰ ስም ምክንያት መከበርን የሚፈልግ ተጫዋች ነው። ሆርጌ ከ ወራቶች በፊት በ አልናስር ቤት አብረውት ከሰሩት ሮናልዶ ጋር በ ፖርቱጋል ብሔራዊ ዳግም ሲጣመሩ ጥሩ ግንኙነት በ ሁለቱ መሀከል ይኖራል ተብሎ ቢጠበቅም ከሰሞኑ በተለይ ከ ኖርዌይ ጋር ተደርጎ በነበረው ጨዋታ ላይ ለ 30 ደቂቃ ያክል ተች ላይኑ ላይ ሲያሟሙቅ ቢቆይም ቀይረው ሳያስገቡት ቀርተው ከዛም አልፎ በ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰአት ላይ የሰጧቸው ግልፍተኛ አስተያየቶች እና በ ውስጥ የተፈጠሩ ግልፅ ያልሆኑ አለመግባባቶች ምክንያት ሮናልዶ ትላንት ከ ኮፐንሀገን በ ግል ጀቱ ስፔን ማድሪድ ገብቷል።
በ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰአት ላይ ሮናልዶን በተጠባባቂ ወንበር ላይ የማስቀመጥ ሙሉ መብት እንዳላቸው ደጋግመው ለመናገር ያልቦዘኑት ሆርጌ በ ብሔራዊ ቡድኑ ስለ አንድ ተጫዋች ብቻ መናገር ስለማይፈልጉ እና 23 ተጫዋቾቻቸውን ወክለው የ ፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድንን እንደሚወክሉ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በ አል ናስር ቤት በነበሩበት ወቅት ላይ ሮናልዶን 18 ጊዜ ቀይረው ማሶጣታቸውን ተናግረው የማይደፈር የሚመስለውን ሮናልዶን በተጠባባቂ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ድፍረት እንዳላቸው በ ጥቂቱም ቢሆን አብሪት የተሞላበት በሚመስል መልኩ ለ ጋዜጠኞች ተናግረዋል። ትላንት ከነዚህ ሁሉ ድራማዎች ቡሀላ ሮናልዶ የተፈጠረውን ወደፊት ግልፅ እንደሚያደርግ ተናግሮ ከ አሰልጣኙ እና ከ ፖርቱጋል ፌዴሬሽን ጋር ንግግር ማድረጉን ተናግሮ ለ ቡድን አጋሮቹ መልካም እድልን ተመኝቶ ካምፑን ለቆ ወቷል።
ሆርጌ እራሱ ሮናልዶ እሳቸው ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ሲመጡ እሱን ካሻቸው በ ተጠባባቂ ወንበር ፣ ከፈልጉ ከነ ጭራሹ በ ጨዋታ ላይ አለማሳተፍ ወይንም ከደጋፊዎች ጋር ተቀምጦ ጨዋታውን እንዲከታተል የማድረግ ስልጣን እንዳላቸው አሳውቋቸው እንደነበር ተናግረው የ ሮናልዶ እዳ እንደሌለባቸው ለማሳወቅ ጥረዋል። ነገሮች በዚሁ ከቀጠሉ የ 41 አመቱ ሮናልዶ ከ ሀገሩ ፖርቱጋል ጋር ዳግም የሚጫወት አይመስልም። የበርካቶች ጥያቄ ታድያ ፊጎ ፣ ዮሴብዮ ወይንም ዴኮ ያላደረጉትን ስኬቶች ( የአውሮፓ ዋንጫ ፣ ኔሸንስ ሊግ 2x ) ማሳካት የቻለው ሮናልዶ ይህ ይገባዋል ወይ??? የሚለው ሆኗል በ ሶሻል ሚድያ ትልቅ ተፅእኖ ያላቸው የ 5 ጊዜ የ ባላንዲዮር አሸናፊው አድናቂዎችም ለ ፖርቱጋል ምላሻቸውን መስጠት የጀመሩት የ ፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን የ ሶሻል ሚድያ ገፆች UNFOLLOW በማድረግ ሆኗል። ለ ሀገሪቱ ከሜዳ ላይ ግልጋሎት ባለፈ ትልቅ የምስል ሽያጭ ትርፍ ሚያስገባው ሮናልዶ በ ኢኮኖሚው ክለቡን ምን ያሀል ይጎዳው ይሆን የሚለውም ጥያቄ ጭሯል።
በ መሳይ ተስፋዬ ✍️

7 days ago