ኢራን የኔታንያሁን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት አወገዘች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያደረጉትን ጉብኝት አውግዟል።
የእስራኤል በቀጠናው ውስጥ መገኘት የሚያስከትለውን በጣም አደገኛ መዘዝ አስመልክቶ ለቀጠናው ሀገራት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የኔታንያሁን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ትንኮሳዊ ሲል የገለጸው ሲሆን፣ እስራኤል በኢራን ላይ የምታካሂደውን ወታደራዊ ጥቃት እንዲሁም በፍልስጤም ግዛቶች እና በሊባኖስ ውስጥ የምታባብሰውን ሁከት ነቅፏል።
የእስራኤል አገዛዝ በኢራን እና በሌሎች የቀጠናው ሀገራት ላይ ያለው ግልጽ ጠላትነት፣ እንዲሁም በኢስላማዊቷ የኢራን ሪፐብሊክ ላይ የሚያደርሰው ተደጋጋሚ ዛቻ ከግምት ውስጥ ሲገባ፤ ሁሉም የቀጠናው ሀገራት የዚህ አይነት መገኘት የሚያስከትለውን መዘዝ በተመለከተ ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸው ምንም ጥርጥር የለውም ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በተጨማሪም የእስራኤል በምዕራብ እስያ መገኘት፣ አለመረጋጋትንና ዋስትና ማጣትን የሚያበረታታ በመሆኑ፣ የቀጠናው መንግስታት የእስራኤልን ተጽዕኖ ሊያስፋፉ የሚችሉ እርምጃዎችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
መግለጫው የወጣው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኔታንያሁ እሁድ ዕለት ሀገሪቱን መጎብኘታቸውን እና ከፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መገናኘታቸውን ካረጋገጡ በኋላ ነው።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል

9 days ago