Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ንብረት የሆነን የኤሌትሪክ ሽቦ የሰረቁ ወንድማማቾች በእስራት ተቀጡ

በአዳማ ከተማ አስተዳደር ሉጉ ክፍለ ከተማ ድሬ ነጋ ወረዳ ጉራራ ከተባለ ስፍራ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ንብረት የሆነ ሁለት መቶ ሜትር የኤሌትሪክ ሽቦን ሠርቀው ለመሠወር የሞከሩ ወንድማማቾች የፍርድ ውሣኔ ማግኘታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሐላፊ ምክትል ኮማንደር ታምራት ጌታሁን ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት፣1ኛ ተከሣሽ ቃሜ ሹሚ 2ኛ ተከሣሽ ሮባ ሹሚ የተባሉ ወንድማማቾች ድርጊቱን ፈፅመዋል።

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ1-49772 ኦሮ በሆነ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ፣ግምቱ ሰላሳ ስድስት ሺሕ ሁለት መቶ ሠባ ሠባት ብር የሆነ የኤሌትሪክ ሽቦ ከቦኩ ክፍለ ከተማ አሮሪቴ ወረዳ በመስረቅ በድሬ ነጋ ወረዳ ለመደበቅ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡በፖሊስ የምርመራ መዝገባቸው በበቂ ማስረጃ ሲጣራ ቆይቶ ለአቃቢ ሕግ የተላለፈ መሆኑን ተናግረዋል።

አቃቢ ሕግም በመሠረተ ልማት ላይ የሚፈፀም ወንጀል በመጥቀስ ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን የተመለከተው የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መስከረም 14-2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱ ወንድማማቾች በሶስት አመት ከሰባት ወር እስራት እንዲቀጡ የተወሠነባቸው መሆኑን ምክትል ኮማንደር ታምራት ጌታሁን ጨምረው ገልፀዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.