Logo
Tikvah-University
ነጻ የስልጠና ዕድል!

ኤልጂ-ኮይካ ተስፋ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ (LG-KOICA Hope TVET College) በኤሌክትሮኒክስ ወይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ዘርፍ ተግባራዊ የሙያ ስልጠና ዕድል አዘጋጅቷል፡፡

የስልጠና መስኮች፦
● የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና (ደረጃ 2 እና 4)
● የሃርድዌር እና ኔትወርክ ጥገና (ደረጃ 3 እና 4)

ዕድሉ ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈ ስልጠና የሚያስገኝ ሲሆን፣ የእንግሊዝኛ እና የኮሪያ ቋንቋ ትምህርት በተጨማሪነት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

የ9ኛ እና 10ኛ ወይም የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል የትምህርት ዝግጅት ያላችሁና በኤሌክትሮኒክስ ወይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፍላጎት ያላችሁ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

ስልጠናው ከሰኞ እስከ አርብ በመደበኛ መርሐግብር የሚሰጥ ሲሆን፣ አመልካቾች የእንግሊዝኛ፣ ሂሳብ እና ፊዚክስ የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡

የማመልከቻ ቦታ፦
አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ ወረዳ 05 በሚገኘው የኮሌጁ ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት ማመልከት ይቻላል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
0116677564 / 0116661829

@tikvahuniversity
8 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.