የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እውቅና ሰጠ
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ዘመን 5ኛ የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን በስኬት ማጠናቀቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በጉባኤው ማጠቃለያም በክልሉ ሁለንተናዊ አበይት ለውጦችን በማምጣት ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማትና መሪዎች የክብራና የእውቅና ሽልማት ተበርክቷል።
በዚህም መሠረት የክልሉ ምክር ቤት «ክልሉን በጥበብ እና በራዕይ ያሻገረ መሪ!» በሚል መሪ ቃል ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ ደስታ ሌዳሞ ልዩ የእውቅና ሽልማት ሰጥቷቸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ላከናወኗቸው የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የሰላም ማስከበር ሥራዎች እንዲሁም ክልሉን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር ላሳዩት አመራር ይህ እውቅና እንደተሰጣቸው ከኮሙኒኬሽን ቢሮው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

9 days ago