Logo
YenetaTube
ቀደም ሲል 21 የነበሩት የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ወደ 6 ዞኖች ተዋቀሩ

ጨፌ ኦሮሚያ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈጻሚ አካላት የማቋቋሚያ አዋጅ ማጽደቁን አስታወቀ። በአዲሱ አዋጅ መሠረት ቀደም ሲል በክልሉ የነበሩ 21 ዞኖች ተጠቃለው ወደ 6 ትላልቅ ዞኖች አዲስ አደረጃጀት ተዘርግቷል።

ይህ የዞኖች አደረጃጀት ሪፎርም በሕግ የተደገፈ ሲሆን፣ አገልግሎትን ከክልል ደረጃ ወደ ዞን፣ ወረዳና ቀበሌዎች በማውረድ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው ተብሏል። በመንግሥት ተቋማት መካከል ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር ኅብረተሰቡን ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ተገልጿል።

በአዲሱ መዋቅር መሠረት ምሥራቅ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ምዕራብ ኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞኖች ተዋቅረዋል። ለእነዚህም አዳዲስ ዞኖች በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የሚመሩ አስተዳዳሪዎች በጨፌው መመደባቸውን ለመረዳት ተችሏል።

Via capital

9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.