Logo
TIKVAH-SPORT
ዋልያዎቹ የመጨረሻ ልምምድ ሰርተዋል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከነገው የሴኔጋል ጨዋታ በፊት የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል።

ዋልያዎቹ ከ 11:30 ጀምሮ ጨዋታው በሚደረግበት ባሕር ዳር ስታዲየም ልምምዳቸውን ሊሰሩ ችለዋል።

በልምምዱ ወቅት :-

- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፤
- የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ዳኛቸው ንገሩ እና
- የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል።

በኢትዮጵያ በኩል በነገው ጨዋታ በረከት ወልዴ በጉዳት እንዲሁም መስፍን ታፈሰ በቅጣት እንደማይሰለፉ ታውቋል።

ኢትዮጵያ ነገ ቀን 10:00 ሰዓት ከሴኔጋል ጋር ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች።

@tikvahethsport      kidusyoftahe
9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.