Logo
FastMereja
Visionary Solutions እና Jordan Beauty Academy የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ።
#fastmereja I ፓን አፍሪካን ኤጁኬሽን ኤንድ ስኪልስ ንዑስ ድርጅት ወይም ሰብ ሲደሪ የሆነው Visionary Solutions እና Jordan Beauty Academy የአጋርነት ስምምነት አድርገዋል።

ዛሬ ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም በተከናወነ ስትራቴጂካዊ ስምምነት ለቀጣይ አምስት አመታት የሚቆይ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ Prometric እና CIDESCO ያሉ አለም አቀፋዊ ደረጃዎች ላይ የተመሰረቱ የውበት ስልጠና እና የሙያ ሰርተፊኬሽን ስርዓቶችን ተደራሽ የሚያደርግ ስምምነት ነው ተብሏል።

በዚህ ስምምነት ምክንያት ተደራሽነቱ ከፍ የሚለው የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና የሀገራችን ባለሙያዎች ለመጀመርያ ጊዜ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የሚገኘው የስራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ተብሏል።

ይህ ጥምረት በኢትዮጵያ ቀዳሚ በመሆን አለም አቀፍ የፈተና እና የምስክር ወረቀት ሰጪ እንዲሁም በከፊል የሰለጠኑና የሰለጠኑ ባለሞያዎችን (semi skilled and skilled workforce) ወደተለያዩ የዉጭ ሃገራት ስምሪትን የሚያሳልጥ ተቋም ፓን አፍሪካን ኤጁኬሽን ኤንድ ስኪልስ ንዑስ አካል ወይም ሰብ ሲደሪ የሆነውን Visionary Solutions የረዥም አመት የውበት ኢንዱስትሪ ቆይታ ካለው እና ከ2500 በላይ ባለሙያዎችን ካፈራው Jordan Beauty Academy ጋር በማገናኘት በዘርፉ ያለውን ባለሙያ ተውዳዳሪነት እንደሚጨምር ተገልጿል።

ስምምነቱ ከስልጠናውም በኋላ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ለመስራት የሚያስችላቸውን ዕውቅና የራሳቸው ማድረግ ያስችላቸዋል።
በVisionary Solutions እና Prometric በኩል የሚገኘውም ዕውቅና ባለሙያዎች የሚኖራቸውን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍ ያደርገዋል።

እያደገ ያለውን የኢትዮጵያ የውበት ኢንዱስትሪም የተሻለ ጥራት ባላቸው ባለሙያዎች እንዲመራና አለም አቀፍ ተፅዕኖው እንዲጎላ ያደርገዋል።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.