Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በእንግሊዝ ምዕራባዊ ክፍል በሚገኘው የፌርፎርድ አየር ኃይል ማዘዣ ጣቢያ አቅራቢያ በተደረገ ሰፊ የፀረ-ሽብር ዘመቻ፣ በፍንዳታ እና ሽ*ብርተኝነት ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ፖሊስ እሁድ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አርባ አምስት ላይ ሶስት አጠራጣሪ ነጭ ተሽከርካሪዎች ወደ አየር ኃይል ጣቢያው እያመሩ መሆኑን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ነው ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ያዋለው። በአሁኑ ሰዓት ጉዳዩን የእንግሊዝ የፀረ-ሽብር ፖሊስ እየመረመረው የሚገኝ ሲሆን፣ አካባቢውም በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ስር ውሏል።

በስፍራው የቦምብ አምካኝ ቡድን የተሰማራ ሲሆን ለጥንቃቄ ሲባል ሰማንያ አምስት ቤተሰቦች ከቤታቸው በአስቸኳይ እንዲወጡ ተደርጎ ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ገብተዋል። ይህ አደገኛ ሊሆን የነበረው ጥቃት የከሸፈው አንዲት የአካባቢው ነዋሪ ባደረገችው ፈጣን የስልክ ጥሪ መሆኑ ታውቋል። ይህችው ነዋሪ ፊታቸውን የሸፈኑ ሰዎች ስታይ ወዲያውኑ ለፖሊስ በማሳወቋ፣ አጥቂዎቹ ያቀዱትን ማንኛውንም ጥፋት እንዳከሸፈች ለቢቢሲ ተናግራለች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለዚህ ጉዳይ አስተያየት ሲሰጡ ግለሰቦቹ ከፍተኛ ጥፋት ለማድረስ አስበው እንደነበርና ለረጅም ጊዜ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቶ መያዛቸውን ገልጸዋል። የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃም በበኩላቸው ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው ህዝብን ለመጠበቅ አስፈላጊው እርምጃ ሁሉ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።

ይህ የፌርፎርድ አየር ኃይል ጣቢያ በቅርቡ አሜሪካ በኢራን ላይ ለፈጸመችው አፀፋዊ ጥቃት እንደ መነሻ ማዕከል ሆኖ ማገልገሉ ይታወሳል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በጥቃቱ ሙከራ የኢራን እጅ አለበት ወይ ተብሎ ለተጠየቁት የእንግሊዝ መከላከያ ሚኒስትር ዌስ ስትሪቲንግ በአሁኑ ሰዓት ስለዚህ ጉዳይ አስተያየት መስጠትም ሆነ መገመት ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው በማለት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ወቅታዊና የተረጋገጡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዘ-ሐበሻ ገጽን ይከታተሉ! ሼር በማድረግ ለሌሎችም ያድርሱ!

10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.