Logo
FBC
‘’ትንፋሼ … የኔ ማስታወሻ’’

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አንዳንድ ድምፆች ዘፈንን ብቻ አያሰሙም፤ ትውስታን ይፈጥራሉ። አንዳንድ ድምፆች የአንድ ሰው ድምፅ ሆነው ይጀምራሉ፤ በጊዜ ሂደት ግን የብዙዎች ሕይወት፣ ስሜትና ትዝታ ይሆናሉ።

ጥላሁን ገሠሠ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ የተለየ ዘመን የፈጠረ ድምፃዊ ነበር። ከ1950ዎቹ ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቲያትር፣ በንጉሠ ነገሥቱ ጥበቃ(በክቡር ዘበኛ) ባንድና በብሔራዊ ቲያትር ያሳለፈው የሙዚቃ ሕይወት ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ተዘርግቷል። በድምጹ ቀለም ለማየት እንሞክር።

ሀገርኛ ቀለም…

የጥላሁን ገሠሠን ሙዚቃ ለየት የሚያደርገው ድምፁ ብቻ አይደለም፤ የዘፈነባቸው ቋንቋዎችም ናቸው። አብዛኛው ሥራው በአማርኛ ቢሆንም፣ በአፋን ኦሮሞም አዚሟል። The Guardian እንደሚገልጸው፣ የሁለት ቋንቋ/ባህል ውጤት የሆነው ጥላሁን፣ በሁሉም የሀገሪቱ ማኅበረሰቦች ዘንድ የተወደደ ድምፃዊ ነው።

በዚህ መንገድ “የሀገር ሽታ”፣ “ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ” የመሰሉ የሀገር ስሜትን የሚያንጸባርቁ ዘፈኖች ከግል ስሜት ወጥተው ወደ የጋራ ትውስታ ይሸጋገራሉ። አንዱ ሰው ሲሰማው “የኔ” ይላል፤ ሌላውም ሲሰማው ተመሳሳይ ስሜት ያገኛል። እዚያ ላይ የግል ማስታወሻ ወደ ሀገራዊ ማስታወሻ ይለወጣል።

ለምሳሌ፣ “የሕይወቴ ሕይወት” በሚለው ዘፈኑ የፍቅርን ቅርበት በሚያሳይ አጭር ሐረግ ውስጥ ሰው ለሚወደው ሰው የሚኖረውን ጥልቅ ስሜት ያስተላልፋል። የዘፈኑ ዋና ሐሳብም ፍቅር ለሰው ሕይወት ራሱ ሕይወት መሆኑን ያመለክታል።
የጥላሁን የአማርኛ ዘፈኖች ብዙ ናቸው፤ እነሱም የፍቅርን፣ የሀዘንን፣ የተስፋንና የማኅበራዊ ሕይወትን ብዙ ገጾች ያሳያሉ። ሆኖም የጥላሁን ሙዚቃ በአማርኛ ብቻ የተገደበ እልነበረም።

“Dammee Maaloo” እና “Shole Ya Nech Tela” ከአፋን ኦሮሞ ሥራዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ። “Dammee Maaloo” በግርድፉ “ውዴ/ውብ ልጅ፣ እባክሽ” የሚል የፍቅር ጥሪ ይይዛል። “Shole Ya Nech Tela” የተቃራኒ ጾታ የፍቅር ዘፈን ሆኖ፣ በጊዜው የኦሮሞ የሙዚቃ ምትን በጥላሁን ድምፅ ለብዙ አድማጮች ያደረሰ ነው። ይህም ሥራው ታዋሽ - ተጠቃሽ ያደርገዋል። ‘’Salaamakaa’’ እና ‘’Ashaam yaa dammee koo’’ እስካሁንም ከቋንቋው ተናጋሪዎች ባሻገር የሄዱ ኪናዊ ሥራዎቹ ናቸው።

እዚህ ላይ የሚታየው ትልቁ ነገር ቋንቋው መቀየሩ አይደለም፤ የሰው ስሜት በተለያዩ ቋንቋዎች እኩል መድረሱ ነው። ሲጠቀለል በሁለቱም ቋንቋዎች የህይወትን ልዩ ልዩ መልኮች ወደ ዜማ እና ግጥም ተርጉሞ ደርሷ-አድርሷል። ይህም አንድ ቀለሙ ነው።

አንድ ሀገር፣ ብዙ ቋንቋዋ፣ አንድ የሰው ልብ።

የጎረቤት ቀለም…

በአማርኛና በኦሮምኛ የዘፈነው ድምጽ፣ ወደ ሱዳን ሲደርስ የሱዳንን ዜማ በመቀበል ከጎረቤት ሕዝብ የሙዚቃ ትውስታ ጋርም ተገናኘ። በ1980ዎቹ ሱዳንን ጎብኝቶ በሱዳን ቴሌቪዢን በመቅረብ: የአህመድ አል-ሙስጠፋን “ሐቢብ አል-ሩሕ­ – ዌይን ያ ናስ’’ ዜማ መዝፈኑ: ይህንን የሙዚቃ ድንበር መሻገሩን በግልጽ ያሳያል። ወደ መጨረሻው ቀለም እንዝለቅ…

አለማቀፋዊ ቀለም…

የጥላሁን ድምፅ ህብረ ብሔራዊ ብቻ አልነበረም። አለማቀፋዊ ጭምር እንጂ። የሙዚቃው ዘይቤም ከአፍሪካና ከዓለም ሙዚቃ ተጽዕኖዎች ጋር የተዋሃደ ነበር። The Guardian የጥላሁንን ድምፅ ከአር-ኤንድ-ቢ፣ ሶልና ጃዝ ጋር የተዋሃደውን የኢትዮጵያ የዳንስ ሙዚቃ ዘመን እንደ ሚያሳይ ይገልጻል። አንዳንድ የድምፅ አቀራረቦቹም የአረብኛ ድምፅ ቅርፅን እንደሚያስታውሱ ይጠቅሳል። ማሳያዎቹም ጩኸቴን ብትሰሙ እና ስግብግብ ጆሮዬ ናቸው።

በመጨረሻም ጥላሁንን ማስታወስ አንድ ድምፃዊን ማስታወስ ብቻ አይደለም። አንድ ዘመንን ማስታወስ ነው። አንድ የሙዚቃ ባህልን ማስታወስ ነው። በተለያዩ ቋንቋዎች የተሰማውን አንድ የሰው ልብ ማስታወስ ነው። ሦስት ሑባሬ/Harmony/ የሰሩ አይነ ግቡ ቀለማትን በአንድ አቡጀዲ አንደማየት…

በሞቱ ጊዜም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የታዩ ሐዘኖች፤ ታዋቂ ሰዎች፣ የፖለቲካ እና የሐይማኖት መሪዎች፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሰጡት የሀዘን መግለጫ: የእርሱ ተፅዕኖ ከሙዚቃ መድረክ በላይ መሄዱን አሳይቷል። ስለሺ ደምሴ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጠው ቃል እናገባድ “የተለያየ የፖለቲካ አቋም ያላቸው ፖለቲከኞች ሁሉ ተቀብለውት ነበር”
ጥላሁን ገሠሠ ሲዘፍን የራሱ ትንፋሽ ነበር፤ ዛሬ ግን ያ ትንፋሽ የትውልድ ማስታወሻ ሆኗል።

‘’ትንፋሼ… የኔ ማስታወሻ’’

በሠራዊት ከበበው

11 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.