ዩኒቲ ብድርና ቁጠባ በሀዋሳ ከተማ ተጨማሪ ቅርንጫፍ አስመረቀ
ዩኒቲ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ከደንበኞች እየጨመረ በመጣው ጥያቄ መሠረት በሀዋሳ ከተማ መሃል አረብ ሰፈር የከፈተውን ተጨማሪ ቅርንጫፍ ዛሬ በይፋ አስመርቋል።
በቅርንጫፉ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሀገረፅሆን አበባ፣ የዩኒቲ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ ሳሙኤል፣ የሲዳማ ክልል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንባሎ ዳንግሶ፣ የሀዋሳ ከተማ ሕብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ዋሬ፣ የብርሃን ባንክ ዲስትሪክት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ግርማ እና የሀዋሳ ንግድ ባንክ ዲስትሪክት ኃላፊ አቶ ወዬሳ ጥላሁን ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ ባንኮች ዲስትሪክት ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ሀገር ሽማግሌዎች፣ የዩኒቲ ደንበኞች፣ የቦርድ አባላትና ማኔጅመንት እንዲሁም የተጋበዙ እንግዶች በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ተገኝተዋል።
የዩኒቲ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተጨማሪ ቅርንጫፉን መክፈቱ በሀዋሳ ከተማ ያሉ ደንበኞች የተቋሙን የቁጠባና የብድር አገልግሎቶች በቀላሉ እንዲያገኙ ከማድረጉ ባሻገር፣ የዩኒቲን የአገልግሎት ሽፋን ለማስፋት ያለውን ትኩረት ያሳያል።

12 days ago