የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ፎከር ቱርክ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መቀስቀሱ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው አስታወቁ።
ቱርክ፣ በትግራይ የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ አደጋውን እንደሚያባብሰው ገልጸዋል። በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ የመንግሥት ወታደሮች መስከረም 13 ቀን በሞርታር በፈጸሙት ጥቃት፣ ሲቪሎች መገደላቸውን የጠቀሱት ቱርክ፣ በትግራይ በአምስት ትምህርት ቤቶች ላይ መስከረም 12 በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሰዎች መገደላቸውንና መቁሠላቸውን ገልጸዋል።
ቱርክ፣ ሁሉም ወገኖች ውጥረቱን እንዲያበርዱና ወደለየለት ጦርነት እንዳይገቡ፣ የሲቪሎችን ደኅንነት እንዲጠብቁና ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
በትግራይ ሕጻናትን ጨምሮ የሚካሄደውን የግዳጅ ምልመላ ቱርክ ያወገዙ ሲኾን፣ የመንግሥት ኃይሎችም የዘፈቀደ ምልመላ ያካሂዳሉ የሚሉ ሪፖርቶች እንዳሉ ጠቅሠዋል።
ዋዜማ
@Yenetube Fikerassefa

13 days ago