Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
በሰሜን ሸዋ ዞን ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የደለቡ የእርድ እንስሳት እንደላሉ ተነገረ።
 
የሰሜን ሸዋ ዞን ለመስቀል በዓል ለአዲስ አበባ እና ለሸገር ከተማ ነዋሪዎች በቀን ከ10 ሺሕ በላይ የእርድ እንስሳት እያቀረበ መሆኑን የዞኑ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
 
በሰሜን ሸዋ ዞን ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የደለቡ ሠንጋዎች፣ 1.4 ሚሊዮን የሚሆኑ በጎች እና  ከ519 ሺሕ በላይ ፍየሎች ባጠቃላይ ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የደለቡ የእርድ እንስሳት  መመዝገባቸውን የዞኑ ግብርና ልማት ፅህፈት ቤት የእንስሣት ዝርያ ማሻሻያና ማደለብ ቴክሎነጂ ማስፋፍያ ባለሞያ ወይዘሮ ሽብሬ ፍቃዴ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
 
የገበያ ዋጋ ለማረጋጋትም በሬ እንደየደረጃቸው ከ150 ሺሕ እስከ 370 ሺሕ ብር፤ በግ እና ፍየል ከ15 ሺሕ እስከ 30 ሺሕ ብር ድረስ እየተሸጡ ይገኛሉም ተብላል ።የመኖ ውድነት፣ የገበያ መዋዠቅ እና የበሽታ አደጋዎች በዋናነት የተጠቀሱ የዘርፉ ችግሮች መሆናቸውን የተናገሩት ባለሙያዋ ወይዘሮ ሽብሬ  አዘውትሮ ክትባት በመስጠት ጥንቃቄ እየተደረገ ነውም ብለዋል።
 
ለበዓሉ ከሚቀርቡት እንስሳት መካከል አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት በጎች እና ሰንጋዎች ሲሆኑ፣ ህብረተሰቡ በጋራ ለሚያከናውነው እርድ ለስላሳ ቀይ ስጋ ያላቸው የኮርማ በሬዎች ተመራጭ መሆናቸው ተገልጿል።

#ዳጉ_ጆርናል
13 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.