Logo
FastMereja
ካምብሪጅ አካዳሚ በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ ያስገነባቸውን የኦዲቶሪየም አዳራሽ፣ የመዋኛ ስፍራ እና የባስኬትቦል ኮርት አስመረቀ።

በሀገር ወዳዱ ዶ/ር ገመቺስ ደስታ የተመሰረተው ካምብሪጅ አካዳሚ፣ በሀገራችን በትምህርት ጥራት እና ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ ካሪኩለም ትምህርት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል እንደሚገኝ ተገልጿል።

አካዳሚው ትናንት በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ ያስገነባቸውን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በይፋ አስመርቋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ወላጆች እና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

በግንባታው ሂደት ድጋፍና መልካም አስተዋፅኦ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦችም ዕውቅና ተሰጥቷል። ከእነዚህም መካከል የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ባለቤት ኢንጂነር ሳሙኤል ይገኙበታል።

የካምብሪጅ አካዳሚ መስራች ዶ/ር ገመቺስ ደስታ በምረቃው ላይ እንደገለጹት፣ ይህ የመሠረተ ልማት ልማት ለሀገር፣ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ እና ለመላው አፍሪካውያን ጥቅም እንዲውል ታስቦ የተገነባ ነው።

ዶ/ር ገመቺስ አክለውም፣ በሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገራት ለሚመጡ ተማሪዎች የሚዘጋጁ ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮችን ማካሄድ እንዲቻል ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሠረት መገንባቱን ገልጸዋል።

“ይህ ተቋም ተማሪዎች በአካላዊ፣ በአእምሯዊ እና በመንፈሳዊ ዘርፎች ሁለንተናዊ እድገት የሚያገኙበት ነው። እግዚአብሔር ልህቀትን ይወዳል፤ ይህንንም ተቋም ለእግዚአብሔር ክብር ገንብተነዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የተገነባው ኦዲቶሪየም ተማሪዎች የተለያዩ ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ የህዝብ ንግግር (Public Speaking)፣ ሙዚቃ፣ ቲያትር፣ ዲቤት እና መሰል ፕሮግራሞችን ለማካሄድ ያገለግላል። እንዲሁም ለስብሰባዎች፣ ለምርቃቶች እና በዶ/ር ገመቺስ የሚሰጡ የአመራርና የአገልግሎት ሥልጠናዎችን ለማካሄድ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

የባስኬትቦል ኮርቱ እና የመዋኛ ስፍራውም ዘመናዊ አቀራረብ ያላቸው ሲሆን፣ የመዋኛ ገንዳው ሙቅ ውሃ የሚያቀርብ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።

ዶ/ር ገመቺስ ደስታ አክለውም፣ መሰል ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች ለመገንባት ዝግጅታቸውን ጨርሰው ጥያቄ አቅርበው ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለትውልድ ጥቅም እና ለሀገር ግንባታ እንዲውል መታሰቡን አካዳሚው ገልጿል።

12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.