ጀፎረ - የአብሮነት የባሕልና የስልጡንነት ተምሳሌት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) "መንገድ አይኑ ይፍሰስ አይባልም ደርሶ፣ የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ" እንደሚባለው፤ መንገድ ሰዎች የማድረስና የመመለስ አገልግሎቱ በዋናነት ይጠቀሳል፡፡
ነገር ግን የመንገድ አገልግሎቱ ከዚህም ይልቃል፤ የማህበረሰብን መስተጋብር የሚፈጥሩ የጋራ ክዋኔዎች የሚከወኑበት፣ ችግሮች በጋራ የሚፈቱበት እንዲሁም ባሕል የሚገለጥበት ነው፡፡
በጉራጌ አካባቢ እንደ መገለጫ ከሚታዩት እንዲሁም ለሌሎች በተምሳሌትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ በአረንጓዴ ሳር የተሸፈነው ውቡ የጀፎረ ጎዳና ነው።
ጀፎረ እንደመተላለፊያ አውራ መንገድ ብቻ አይቆጠርም፤ ይልቁንም ማህበረሰቡ ለዘመናት የጋራ ጉዳዮችን የሚከውንበት ስፍራ ጭምር እንጂ።
በቤቶች መካከል የሚተው ክፍት ቦታ ብቻ ሳይሆን፤ በዓላት የሚከበሩበት፣ የሰርግ መከወኛና፤ ሀዘን በጋራ የሚገለፅበት፣ ህጻናት የሚቦርቁበት፤ አዋቂዎችም መፍትሔ ሽተው የሚመክሩበት፤ ማህበራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ስፍራ ነው፡፡
ከቀደሙት ጊዜያት ጀምሮ ማህረሰቡ ባልተጻፈ፤ ነገር ግን እርስ በእርሱ በሚግባባበት ህግ ተመስርቶ መኖሪያ ቤቶቹን ሲሰራ የጋራ መሰብሰቢያ ለሆነው ጀፎረ 60 ሜትር ያህል ቦታ ክፍት ይተዋል፡፡
ከዚህ መንገድ ላይ ቀንሶ ወደ ራስ ማድረግ በማህበረሰቡ ዘንድ ያስወግዛል፤ እንደ ነውርም ይቆጠራል፤ በመሆኑም ስንዝር መሬት ለመስረቅ የሚደፍር እንደሌለ ነው የሚነገረው፡፡
ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፉ ከመጡ የጉራጌ ባሕልና ተውፊቶች በተጨማሪ አካባቢን በጋራ ጠብቆ ለጋራ የማቆየት መልክ የሆነው ጀፎረም በተምሳሌትነት የሚነሳ ነው፡፡
በተለይም የመስቀል በዓል አከባበርና ጀፎረ የማይነጣጠሉ የአካባቢው መገለጫዎች ናቸው።
የአካባቢው ተወላጆች ወቅቱን ጠብቀው ያላቸውን ቋጥረው በዓሉን ለማክበር ሲገቡ፤ ተራርቀው ከነበሩት ጋር የሚገናኙበት ነው፡፡
በተጨማሪም ከጎረቤቶቻቸው ጋር ያወጉበታል፤ እንግዶቻቸውን ጋብዘው በዓሉን ተሰባስበው ያከብሩበታል።
ደግሞም ለሀገር ሰላምን፣ ለሕዝብ አንድነትን የሚመኙበት፤ የሚመራረቁበትና ኬር የሚሉበት ነው፡፡
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ እየተገበረች ለምትገኘው የገጠርና የከተማ ኮሪደር ልማትም በምሳሌነት የሚጠቀስ ከዘመን የመቅደምና የስልጡንነት ምልክት ነው፡፡
በመሆኑም ጀፎረ የጉራጌ ማሕበረሰብ በዓሉን የሚያከብርበት ብቻ ሳይሆን፤ የአብሮነት፣ በጋራ የመስራትና የመብላት እንዲሁም ችግርን የመፍታት፣ ደስታና ሀዘንን የመጋራት ወርቃማ ባሕሉን ጭምር የሚገልጥበት ነው፡፡
በቤተልሔም ግርማ
u1300u134eu1228 - u12e8u12a0u1265u122eu1290u1275 u12e8u1263u1215u120du1293 u12e8u1235u120du1321u1295u1290u1275 u1270u121du1233u120cu1275
u12a0u12f2u1235 u12a0u1260u1263u1363 u1218u1235u12a8u1228u121d 15u1363 2019 (u12a4u134d u12a4u121d u1232) \

13 days ago