(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሱዳን፣ በሶማሊያ እና በየመን እየተካሄዱ ያሉትን አውዳሚ ጦርነቶች ተከትሎ፣ አሁን በኢትዮጵያ ያገረሸው መጠነ ሰፊ ግጭት መላውን ቀጠና ወደ እሳት አዘቅት የሚከት "እጅግ አስፈሪ ቅዠት" መሆኑን ዓለም አቀፉ የችግር ጊዜ ተንታኝ ቡድን (Crisis Group) አስጠነቀቀ። የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት የጦርነት ዓመታት ካሳለፈው መከራ አንጻር፣ አዲሱ ጦርነት ሊያስከትል የሚችለው ሰብዓዊ ቀውስ ዘግናኝ ከመሆኑም በላይ፣ ሌሎች ጎረቤት ሀገራትን ወደ ጦርነቱ በማስገባት የአፍሪካ ቀንድን ሙሉ በሙሉ ሊያወድም የሚችልበት ዕድል እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል። ይህንን አደጋ ለማስቀረት አሁንም ጠባብ የዲፕሎማሲ ዕድል ቢኖርም፣ አፋጣኝ ጣልቃ ገብነት ካልተደረገ ይህችም በር በቅርቡ ልትዘጋ ትችላለች።
ይህ የቅዠት ስጋት እውን መሆን የጀመረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የአማራ ፋኖ ታጣቂዎች መንግስትን ለመጣል የጋራ ጥምረት ፈጥረው ከሴፕቴምበር 23 ጀምሮ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ነው። ባለፈው ጦርነት ፊት ለፊት ሲዋጉ የነበሩት እነዚህ ኃይሎች መጣመራቸው፣ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ያፈረሰ ሲሆን፤ የፌደራል መንግስቱም በበኩሉ የድሮን ጥቃቶችን በማጠናከር በሰሜን ወሎ እና በትግራይ-አፋር ድንበር ላይ ከባድ ውጊያዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። የትግራይ ኃይሎች በመቀሌ፣ አክሱም እና ሽሬ ያሉትን አየር ማረፊያዎች ያለምንም ተኩስ ሲቆጣጠሩ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ክልሉ የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ አቋርጧል።
የጉዳዩ አሳሳቢነት ከኢትዮጵያ ድንበር የዘለለ ሆኗል። ሪፖርቱ እንደሚያስረዳው... የፕሪቶሪያው ስምምነት አግልሎኛል የምትለው ኤርትራ አሁን ከቀድሞ ጠላቷ ህወሓት ጋር በድብቅ የተቧደነች ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ደግሞ አስመራን የተቃዋሚዎች ጥምረት አስተባባሪ አድርጋ ትከሳለች። ከዚህም ባለፈ በሱዳኑ የእርስ በርስ ጦርነት ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን (ሲደግፉ፤ ግብጽ፣ ኤርትራ እና ሳዑዲ አረቢያ የሱዳንን መደበኛ ጦር ይደግፋሉ። የሱዳን ጦር የትግራይ ተዋጊዎችን አስጠልሏል በሚል ቁጣ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት፣ ፋ*ኖን እና ህወሓትን ጨምሮ ይህንን የተወሳሰበ የጥቅም ትስስር ተከትሎ ጦርነቱ የሁለቱን ሀገራት (የኢትዮጵያ እና ሱዳን) ድንበር በማቋረጥ ሊቀላቀል እንደሚችል ስጋቱን አባብሶታል።
መላው የአፍሪካ ቀንድን ሊያነድ የተቃረበውን ይህንን ሰፊ ጦርነት ለማስቆም፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪዎች (እንደ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ያሉ)፣ የኬንያ መሪዎች፣ አሜሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገራት (UAE እና ሳዑዲ) አፋጣኝ ጫና መፍጠር አለባቸው። ጦርነቱ ወደ ለየለት እና ከቁጥጥር ውጭ ወደሆነ ቀጠናዊ እልቂት ከማምራቱ በፊት፣ የትግራይ ኃይሎች ጥቃታቸውን አቁመው ወደ ድርድር እንዲመጡ፣ የፌደራል መንግስቱም ወደ ትግራይ መጠነ ሰፊ የእግረኛ ጦር ከማስገባት እንዲቆጠብ እና ለድርድር ጊዜ እንዲሰጥ አስቸኳይ የዲፕሎማሲ ስራ ይጠይቃል።
(u12d8-u1210u1260u123b u12dcu1293) u1260u1231u12f3u1295u1363 u1260u1236u121bu120au12eb u12a5u1293 u1260u12e8u1218u1295 u12a5u12e8u1270u12abu1204u12f1 u12ebu1209u1275u1295 u12a0u12cdu12f3u121a u1326u122du1290u1276u127d u1270u12a8u1275u120eu1363 u12a0u1201u1295 u1260u12a2u1275u12eeu1335u12eb u12ebu1308u1228u1238u12cd u1218u1320u1290 u1230u134a u130du132du1275 u1218u120bu12cdu1295 u1240u1320u1293 u12c8u12f0 u12a5u1233u1275 u12a0u12d8u1245u1275 u12e8u121au12a8u1275 \

13 days ago