ቀነኒሳ በበርሊን ማራቶን አይሳተፍም
#ethiopia | የቀድሞው የ5,000 እና 10,000 ሜትር የዓለም ክብረወሰን ባለቤት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከነገ የሚካሄደው የBMW በርሊን ማራቶን ውጪ ሆኗል።
አትሌቱ በዝግጅት ላይ እያለ በግራ እግሩ የአኪሊስ ጅማት ጉዳት እንዳጋጠመው የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል። በመሆኑም በበርሊን ማራቶን እንደሚሳተፍ ከተገለጸ ከአንድ ሳምንት በኋላ በመጨረሻው ሰዓት ከውድድሩ ለመውጣት ተገዷል።
ቀነኒሳ በ2019 በበርሊን ማራቶን 2:01:41 በመግባት የኢትዮጵያ የማራቶን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል። ይህም አሁንም ከዓለም ምርጥ የማራቶን ውጤቶች መካከል ይገኛል።
በዚህ ዓመት የBMW በርሊን ማራቶን የወንዶች ውድድር ቀነኒሳን ጨምሮ በርካታ ተጠባቂ አትሌቶች በጉዳት ከውድድሩ ውጪ መሆናቸው ተገልጿል።
የ2025 የበርሊን ማራቶን አሸናፊ እና የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ሳባስቲያን ሳዌም በጉዳት ምክንያት ዘንድሮ አይሳተፍም።
በሴቶች ምድብ ደግሞ የኢትዮጵያዋ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በበርሊን ማራቶን አዲስ የዓለም ክብረወሰን ለማስመዝገብ ትሮጣለች። አሰፋ እ.ኤ.አ. በ2023 በበርሊን 2:11:53 በመግባት የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገቧ ይታወሳል።
በ2026 የBMW በርሊን ማራቶን ከ162 አገራት የተውጣጡ ከ84,000 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ዋናው የማራቶን ውድድር ነገ እሁድ ይካሄዳል።
አንተነህ ብርሃኔ
የአትሌቲክስ (ሩጫ) ስፖርት ዘጋቢ

12 days ago