Logo
AHADU RADIO FM 94.3
በጉራጌና በደቡብ ክልሎች መስቀልን ለማክበር ለሚጓጓዙ ሰዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይገጥማቸው ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ

መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም.  (አሐዱ ሬዲዮ) በጉራጌ እና በደቡብ ክልሎች መስቀል ለማክበር ለሚጓጓዙ ሰዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይገጥማቸው ዝግጅት ተጠናቆ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮ አፍሪካ የሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር አስታውቋል ።

የማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ መኮንን ወርቄ የመስቀል በዓልን ለማክበር ወደ ተለያዩ አከባቢዎች ለሚጓጓዙ ሰዎች በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

በመስቀል በዓል ወቅት በርካታ ሰዎች ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ስለሚያከብሩ የትራንስፖርት አገልግሎቱ እና የተጓዦችን ቁጥር ባመጣጠነ መልኩ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚቀርብ ተናግረዋል ።

በተለይም የመስቀል በዓል ሳምንት ሲቀረው አብዛኛውን ሰዎች ወደ ተለያዩ ቦታ ስለሚጓዙ ከሳምንት ቀደም ብሎ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አብራርተዋል ።

የመስቀል በዓልን አስመለክቶ አንድ ቦታ ላይ በቡድን ለሚያከብሩ ሰዎችም የትራንስፖርት አማራጮችን እንዲጠቀሙ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል ።

በማህበሩ ስርም በአሁኑ ወቅት 250 ተሽከርካሪዎች እንዳሉና እነዚህ ተሽከርካሪዎች የአገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በተመስገን ተጋፋው

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.