ጠንቋይ ነኝ ባለ ሰው ምክር ተነሳስቶ የ5 ዓመት ህፃን ልጅን ወንዝ ውስጥ በመክተት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ እስራት ተቀጣ
ድርጊቱን የፈጸመው የቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ኢልኩሌ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ጉዮ ገልማ ገንዲ የተባለ የ30ዎቹ አጋማሽ ወጣት ሲሆን አዋቂ ወይም ጠንቋይ ነኝ ባለ ሰው ምክር ተነሳስቶ የ5 ዓመት ህፃንን በመግደሉ የ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንደተፈረደበት የቦረና ዞን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ጉዮ ከልጅነቱ እስከ ጉልምስናው ጠንክሮ ቢሠራም የሚፈልገው ደረጃ ላይ ባለመድረሱና ከእርሱ በኋላ የተነሱት በሀብት በመቅደማቸው የተነሳ በተሰማው ከፍተኛ የመማረር ስሜት አቋራጭ መንገድ ፍለጋ ወደ አንድ አዋቂ ዘንድ ያቀናል፡፡
አዋቂ ነኝ ባዩም የሠራኸው ሁሉ የተባረከ እንዳይሆን መድኃኒት ተሠርቶብሃል፤ ይህንን ለማክሸፍ የ5 ዓመት ወንድ ልጆችን የምሰጥህን ውሃ ማጠጣት አለብህ የሚል አደገኛ ምክር ይሰጠዋል። ምክር የተሰጠው ጉዮም ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት ተኩል ላይ ጌመቹ ዲዳ የተባለው የ5 ዓመት ህፃን የተሰጠውን ውኃ እንዲጠጣ ቢያስገድደውም ህፃኑ በመቃወሙ፣ በንዴት አንገቱን አንቆ ኤላ ወደሚባል ወራጅ ወንዝ ውስጥ በመወርወር ሕይወቱ እንዲያልፍ ያደርገዋል።
የቦረና ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዲባ ቦሩ እንደገለጹት፤ ከሁለተኛው ህፃን በተገኘ ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ወዲያውኑ ተንቀሳቅሶ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ያዋለው ሲሆን ምርመራውን አጠናቆ ድርጊቱ መፈጻሙን ያረጋግጣል።
ጉዳዩን መርምሮ የተመለከተው የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም፤ ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ጉዮ ገልማ ገንዲ በአጉል እምነት ተነሳስቶ በህፃኑ ላይ የፈጸመው ድርጊት ከባድና ጨካኝ በመሆኑ በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል

14 days ago