Logo
YeneTube
በላሊበላ ገዳም አቅራቢያ እየተተኮሱ ያሉ ከባድ መሣሪያዎች በታሪካዊው ህንፃ ላይ ላይ ሥጋት ደቀኑ

በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በዓለም ቅርስነት በተመዘገበችው ላሊበላ በሚገኙ ገዳማት አካባቢ በከባድ መሣሪያዎች የሚካሄደው የተኩስ ንዝረት ታሪካዊ ቅደሳቱን እየናጣቸው እንደሚገኝ መሠረት ሚድያ ሰምቷል።

በገዳሙ ያሉ ምዕመናን እንደገለጹት በዙሪያው በሚተኮሱ ከባድ መሣሪያዎች ምክንያት የላሊበላ ገዳም በላይ ያለው ጣሪያና የታችኛው መሬት እያረገረገ ይገኛል።

ምዕመናንና የኃይማኖት አባቶች ይህ ታሪካዊና የተቀደሰ ስፍራ አደጋ ውስጥ መውደቁን በመግለጽ የኦርቶዶክሳውያንና የመላው ህዝብ ድምፅ አሁኑኑ ሊሰማ እንደሚገባና ቅርሱ ከፈረሰ በኋላ ማዘን ጥቅም እንደሌለው በማስገንዘብ አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

@Yenetube Fikerassefa
15 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.