Logo
YeneTube
በኢትዮጵያ ያለው የታጣቂ ቡድኖች ጥምረት እና የድሮን ጥቃቶች አስቦኛል - የተባበሩት መንግስታት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአዲሱን የታጣቂ ቡድኖች ጥምረት መመሥረት፣ የቀጠለውን የጸጥታ ችግር እና የድሮን ጥቃት ዘገባዎችን በመጥቀስ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለፀ።

ትላንት በተካሄደው የተመድ ዕለታዊ የዜና መግለጫ ላይ የተቋሙ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ እስቴፋን ዱጃሪክ እንደተናገሩት፣ ተመድ በኢትዮጵያ ውጥረት በተባባሰበት በዚህ ወቅት በተከሰቱ አዳዲስ ኩነቶች «ጥልቅ ስጋት» እንደገባው አስታውቀዋል።

ቃል አቀባዩ «ውጥረት በነገሠበት በዚህ ወቅት፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን ይበልጥ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ወይም ንግግሮች እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን» ብለዋል።

አክለውም «ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን አይፈታም፤ ወይም መሠረታዊ ቅሬታዎችን አይመልስም» ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ ወገኖች ለውይይትና ለንግግር ዳግም ቁርጠኝነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

@Yenetube Fikerassefa
17 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.