በቤንች ሸኮ ዞን በህይወት እያለ የራሱን የሐዘን ባነር ያዘጋጀው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦካ ቀበሌ በህይወት እያለ «ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል» የሚል የሐዘን መግለጫ ባነር ያዘጋጀ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።
የክልሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እንዳስታወቁት ግለሰቡ የራሱን ፎቶግራፍ በመጠቀም የህዘን መግለጫ ባነር አዘጋጅቶ በማሰራጨቱ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።
ድርጊቱ በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥና አለመረጋጋት መፍጠሩን የገለፁት ኢንስፔክተሩ መሰል የህሰት መረጃዎች ህዝብን የሚያሳስቱና ሰላምን የሚያደፈርሱ በመሆናቸው ማኅበረሰቡ የሚደርሱትን መረጃዎች ሳያጣራ እንዳያምን አሳስበዋል።ፖሊስ የህዝብን ሰላምና ሥነ-ልቦና ሊያውኩ የሚችሉ መሰል ድርጊቶችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል ተብሏል።
ሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

16 days ago