ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የፉላ ግድብን ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኗን ገለጸች
ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የሚገነባውን የፉላ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ለማስጀመር ዝግጅት እያደረገች መሆኗን የሀገሪቱ የኃይል እና ግድቦች ሚኒስቴር አስታወቀ።
በጁባ በተካሄደው 7ኛው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኮንቬንሽን (GLC 2026) ይፋዊ የሚዲያ ማስጀመርያ ስነ-ስርዓት ላይ የተናገሩት የኃይል እና ግድቦች ሚኒስትር አጎክ ማኩር፣ ሀገራቸው የግድቡን ግንባታ ለማካሄድ ከግብፅ በኩል የሚመጣ ምንም ዓይነት ፍራቻ እንደሌላት ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም ደቡብ ሱዳን በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመች ያለችው ከአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟ አንድ በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ማቆየቱን አስረድተዋል።
በዕቅድ ላይ ያለውና በኒሙሌ አካባቢ የሚገነባው የፉላ ግድብ 1,800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የደቡብ ሱዳንን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ማሟላት ከማስቻሉም በላይ ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ትርፍ ኃይል እንደሚያመነጭ ተገልጻል።
አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለሎጂስቲክስ እና ለጠቅላላ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ሚኒስትሩ፣ ሀገሪቱ በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም (August 2026) በጁባ በሚገኘው ፒራሚድ ኮንቲኔንታል ሆቴል የምታስተናግደው የሎጂስቲክስ ኮንቬንሽን የዘርፉን ባለሙያዎች፣ ኢንቨስተሮችን እና ፖሊሲ አውጪዎችን እንደሚያገናኝ ተናግረዋል።
@TikvahethMagazine

20 days ago