(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ መንግስት በኢራን የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ የጣለው የተስፋፋ ማዕቀብ ወደ ተግባር ሊለወጥ ሰዓታት ሲቀሩት፣ ከኢራን ወደ ኢራቅ እና ኦማን ዋና ከተሞች የሚደረጉ በረራዎች ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ መቋረጣቸው ተገለጸ።
የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል የሀገሪቱን ሲቪል አቪዬሽን ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የባግዳድ እና የሙስካት ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች ከእንግዲህ የኢራን አውሮፕላኖችን እንደማይቀበሉ አሳውቀዋል። ሆኖም ወደ ኢስታንቡል እና ሌሎች መዳረሻዎች የሚደረጉ ዓለም አቀፍ በረራዎች በመደበኛ የጊዜ ሰሌዳቸው መሰረት ያለምንም ችግር እየቀጠሉ መሆናቸው ተገልጿል።
ይህንን የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ጫና ለማቃለል የኢራን አቪዬሽን ባለስልጣናት ወደ ባግዳድ ይደረግ የነበረውን በረራ በርካታ የኢራን መንፈሳዊ ተሳላሚዎች ወደሚጓዙባት ናጃፍ ከተማ ለማዞር ድርድር መጀመራቸው ተጠቁሟል። በተጨማሪም ከኦማን መንግስት ጋርም አዲስ ድርድር እየተደረገ መሆኑን ኢስና (ዜና ወኪል አስነብቧል።
የኢራቅ መንግስት የአሜሪካንን እገዳ ተግባራዊ ስለማድረጉ በይፋ ያወጣው መግለጫ ባይኖርም፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባግዳድ የአሜሪካንን ውሳኔ ለመቀበል መገደዷን ለፈረንሳይ ዜና ወኪል አረጋግጠዋል።
አሜሪካ በዚህ ወር መጀመሪያ የኢራንን አቪዬሽን ዘርፍ በጥቁር መዝገብ ውስጥ ያስገባች ሲሆን፣ ከኢራን አየር መንገዶች ጋር አብሮ በሚሰራ ማንኛውም የውጭ ተቋም ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል አጠንክራ ዝታለች። የአሜሪካው የገንዘብና ግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት ትናንት እንዳስታወቁት፣ ማዕቀቡ ተግባራዊ መደረግ ሲጀምር የኢራን አየር መንገዶች እጅግ ከባድ ፈተና ውስጥ ይወድቃሉ።
ሚኒስትሩ ለሲ.ኤን.ቢ.ሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ "ሁሉም የኢራን አየር መንገዶች በዓለም ዙሪያ በራቸው ይዘጋል" ሲሉ የአሜሪካን የኢኮኖሚ ማነቆ ጫና ክብደት አጉልተው ገልጸዋል። ይህ ውሳኔ አሜሪካ የኢራንን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማግለል የምታደርገውን የኢኮኖሚ ጦርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ መሆኑን ያሳያል።

15 days ago