(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA) ጎንዮሽ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከአሜሪካው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሲያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይት አድርገዋል። አቶ ጌታቸው በለቀቁት መግለጫ፣ ከአሜሪካው ከፍተኛ ባለስልጣን ጋር በቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ዙሪያ በቅርበት ለመስራት መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል።
በውይይታቸው ወቅት ሁለቱ ወገኖች በግንቦት 2026 በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደውን የኢትዮ-አሜሪካ መዋቅራዊ ውይይት (Structured dialogue) መነሻ በማድረግ መምከራቸው ተገልጿል። በዚህም መሰረት በኢኮኖሚ ብልጽግና፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ እና የጸጥታ ትብብር፣ እንዲሁም በቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አቶ ጌታቸው አረጋግጠዋል።
"በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA) የጎንዮሽ መድረክ ላይ፣ ከአሜሪካው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሲያ ጋር የሁለታችንንም የጋራ ፍላጎት በሚያንጸባርቁ የቀጣናችን የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ወሳኝ ጉዳይ ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገናል።
በውይይታችንም፣ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ይበልጥ ማሳደግ እና ማጎልበት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በጽኑ አጽንኦት ሰጥተናል። ከዚህም ባሻገር፣ ባለፈው ግንቦት 2026 በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኢትዮ-አሜሪካ መዋቅራዊ ውይይት ላይ በተነሱት የኢኮኖሚ ብልጽግና፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ የመከላከያና የጸጥታ ትብብር፣ እንዲሁም የቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ በቀጣይ አብረን በምንሰራቸው ተግባራት ዙሪያ በስፋት መክረናል። በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን መረጃዎችን በቋሚነት በመለዋወጥ እና በጋራ በመቆም በቅርበት አብረን ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰናል።" ሲሉ ጌታቸው ገልጸዋል።
የዚህ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ትልቁ ፖለቲካዊ አንድምታ፣ በኢትዮጵያ እና በቀንዱ ፖለቲካ ላይ እየታየ ካለው አዲስ የኃይል አሰላለፍ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ መሆኑ ነው። በአንድ በኩል በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን ከኤርትራ መንግስት ጋር ጭምር "የህልውና ጥምረት" ፈጥሮ የፌደራል መንግሥቱን በጦርነት ለመውጋት እያንዣበበ ባለበት በዚህ ወሳኝ ሰዓት፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የፌደራል መንግሥቱን ወክለው በኒውዮርክ ከአሜሪካ መንግሥት ጋር በመከላከያ፣ በጸጥታ ትብብር እና በቀጣናዊ ሰላም ዙሪያ መምከራቸው ከፍተኛ ትርጉም አለው።

16 days ago