ገዳ ባንክ በበጀት ዓመቱ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የትርፍ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ
ገዳ ባንክ 5ኛውን መደበኛ የባለአክሲዮኖች
ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት በበጀት ዓመቱ ባሳየው ጠንካራ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ከታክስ በፊት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጿል።
በጉባኤው ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ የባንኩን የካፒታል አቅም ለማሳደግ የተገኘውን ትርፍ ወደ ካፒታል ለማዋደድ እና በቀጣይም የካፒታል መጠኑን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ እንደገለጹት፣ ባንኩ ሥራ በጀመረ በ3 ዓመት ከ6 ወር አጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ የደንበኞቹን ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ችሏል።
እንደ ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ ባንኩ በበጀት ዓመቱ 1 ቢሊዮን 5 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት 444 ሚሊዮን ብር አንጻር ሲነጻጸር ከ120 በመቶ በላይ ከፍተኛ ዕድገት ያሳየበት ነው።
በተመሳሳይ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት የ64 በመቶ ዕድገት በማሳየት 16.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል። የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በ65 በመቶ፣ አጠቃላይ ገቢው በ77 በመቶ፣ እንዲሁም ወጪው በ55 በመቶ ያደጉ ሲሆን፤ የተፈቀደ ካፒታሉ 7 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1.65 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጻል።
Seledadotio

18 days ago