አርሲ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን ነባር ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሲ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ4 ሺህ 300 በላይ ነባር ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፍቃዱ ምትኩ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲቲው ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በቂ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ተማሪዎች በንጹሕ፣ ምቹና ማራኪ የትምህርት ከባቢ ውስጥ ተምረው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲው የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የተማሪ ቅበላ ቅድመ ዝግጅት ሥራ ቀድሞ የተጀመረ ሲሆን፤ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻዎችን ከማደስ እስከ ግብዓት ማሟላት ድረስ ያሉ ተግባራት በትኩረት ሲሰሩ መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡
በጋሻው አርጋ

24 days ago