(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ጥንታዊ መፅሀፍ ቅዱስ ለጨረታ መቅረቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህ ጨረታ ከሴፕቴምበር 13 አንስቶ እስከ ሴፕቴምበር 18 እንደሚቆይ የተገለፀ ሲሆን አሁን የጨረታው ሂደት ውስጥ ይገኛል፡፡ ጨረታውን ያወጣው ‹‹ኢንሊብሪስ›› የተሰኘው አንድ የአውሮፓ ቅርስ ሻጭ ድርጅት በአቡዳቢ በሚገኘው ቅርንጫፉ አማካኝነት ነው፡፡ ድርጅቱ ቀደም ሲል በድረ ገፁ እንዳስታወቀው የዚህ ጥንታዊ መፅሀፍ ቅዱስ የጨረታ መነሻ ዋጋ 250,000 ዩሮ ወይንም 214,500 ፓውንድ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ይህንን ቀይሮታል፡፡ ዋጋውን ‹‹ሲጠየቅ የሚገለፅ›› (ፕራይስ ኦን ሪኩዌስት) በሚል አስፍሯል፡፡
የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ንብረት የሆነው ጥንታዊ መፅሀፍ ቅዱስ በብራና የተፃፈና በግእዝ ቋንቋ የቀረበ ሲሆን 218 ገፆች ያሉት ነው፡፡ በውስጡም 235 ምስሎች የተካተቱበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሁለቱ ሙሉ ገፅ የሚሸፍኑ፣ 220ዎቹ ግማሽ ገፅ የሚሸፍኑና 13ቱ መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ ምስሎች ናቸው፡፡ በግምት ከ1730 እስከ 1740 ባሉት አመታት ውስጥ እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡ መፅሀፉ ሙሉውን የሉቃስ ወንጌልና የዮሀንስ ወንጌል ክፍሎች ያካተተ መሆኑን አጫራቹ ድርጅት አስረድቷል፡፡ እንድርጅቱ ይህ የብራና መፅሀፍ ሲዘጋጅ ሁለት ጥራዞች ያሉት ስብስብ አካል ነበር፡፡
የማቲዮስና የማርቆስ ወንጌሎችን ያካተተው ሌላኛው ጥራዝ አሁን በጀርመን በሚገኘው ባቫሪያን ስቴት ቤተ መፅሀፍት ውስጥ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡ ይህ የብራና መፅሀፍ ቅዱስ ከአቻው ጥራዝ ጋር የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ቤተሰብ ንብረት መሆኑን የጠቀሰው ድርጅቱ እ.ኤ.አ በ1868 በጄኔራል ሮበርት ናፒር የሚመራው የብሪታኒያ ጦር መቅደላን በተቆጣጠረበት ወቅት ከተዘረፉት በርካታ ንብረቶች ውስጥ እንደሚካተት አስረድቷል፡፡ ‹‹የጎንደር ወንጌል›› የሚል መለያ የተሰጠው ይህ መፅሀፍ ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ የጄኔራል ናፒር ንብረት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከዚያም የቦምቤይ አስተዳዳሪ ለነበሩት ዊሊያም ሮበርት የተላለፈ ሲሆን በ887 ደግሞ የጥንታዊ መፅሀፍት አከፋፋይ በሆነው ኳሪች አማካኝነት ወደሬቨረንድ ሮድዌል ስብስቦች ገብቷል፡፡ በመቀጠል በፒት ሪቨርስ ሙዚየም ውስጥ ከቆየ በኋላ በኖቬምበር 1990 ከሙዚየሙ መውጣቱ ተገልጿል፡፡ ይህንን ተከትሎ የኖርዌይ ባለሀብት የሆኑት ማርቲን ሾየን ይህንን ታሪካዊና ሀይማኖታዊ መፅሀፍ ገዝተው እስከ 2002 አ.ም በእጃቸው አቆይተውታል፡፡ በመቀጠል መፅሀፉን የገዙት እንግሊዛዊው ቢሊየነርና የቅርስ ሰብሳቢ ሰር ፖል ራዶክ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን እስካ 2017 በእኚህ ባለሀብት ቤተመፅሀፍት ውስጥ የቆየ ነው፡፡ እንግሊዛዊው ቢሊየነር ደግሞ በቅርስና ጥንታዊ የእጅ ፅሁፎች ሽያጭ ላይ ለተሰማሩት ሳም ፎግ አስተላልፈውታል፡፡
ለ158 አመታት በተለያዩ ሙዚየሞች፣ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች እጅ ሲዘዋወር የቆየው ይህ መፅሀፍ ለጨረታ መቅረቡን ተከትሎ የ‹‹ኢንሊብሪስ›› ቃል አቀባይ ለቮይስ በሰጡት መግለጫ ንብረቱ የኢትዮጵያ መሆኑን ታሪኩ እንደሚናገር ገልፀው ቢሆንም የባለቤትነት መብት እንዳላቸው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ ጨረታው እንዳለ ሆኖ ከኢትዮጵያ በኩል የመግዛት ሀሳብ ካለ ግን ‹‹በበጎ ፈቃደኝነት›› በተመጣጣኝ ዋጋ ለመሸጥ ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ዘግበን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ይህን ሀሳብ ውድቅ አድርጎታል፡፡ የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ከመቅደላ ተዘርፎ የተወሰደ ንብረት በመሆኑ ለኢትዮጵያ መመለስ እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡ ለአጫራቹ ድርጅት ጨረታውን እንዲያቆም ይፋዊ ጥያቄ መላካቸውን ገልፀው ‹‹ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደኢትዮጵያ መመለስ አለበት›› ብለዋል፡፡

22 days ago