አፍሪካውያን ቻይናውያን ነጋዴዎች ይውጡልን እያሉ ነው
#ethiopia | በናይጄሪያ ሌጎስ የንግድ ማዕከል የሚሰሩ የሀገር ውስጥ ነጋዴዎች፣ ቻይናውያን ነጋዴዎች በችርቻሮ ንግድ ዘርፍ ውስጥ ገብተው በቀጥታ ለደንበኞች ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ እቃዎችን ማቅረባቸውን በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።
ነጋዴዎቹ "ቻይናውያን ለቀው ይውጡ" የሚሉ መፈክሮችን በማንገብ ያካሄዱት ተቃውሞ የፖሊስን ትኩረት የሳበ ሲሆን የናይጄሪያ ባለስልጣናት ደግሞ የተቃውሞው አስተባባሪዎች ለእስር ሊዳረጉ እንደሚችሉ አስጠነቅቀዋል።
ይህ በቻይናውያን ነጋዴዎች እና በሀገር ውስጥ ስራ ፈጣሪዎች መካከል የተነሳው የንግድ ውድድር ስጋት በናይጄሪያ ብቻ የተወሰነ አይደለም።
መሰል ቅሬታዎች እንደ ጋና እና ኡጋንዳ ባሉ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም እየተስተዋሉ ይገኛሉ። የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶም በቅርቡ ባደረጉት ንግግር፣ ቻይናውያንን ጨምሮ የውጭ ሀገር ዜጎች በጎዳና ላይ ንግድ እና በትንንሽ የችርቻሮ ዘርፎች ውስጥ ገብተው ከሀገር ውስጥ ዜጎች ጋር መፎካከር እንደሌለባቸው ገልጸው ነበር።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

22 days ago