ሀገራዊ ቁርጠኝነትን ያረጋገጡ ታላላቅ ፕሮጀክቶች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት በቅርብ ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበው የታላላቅ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ሀገሪቱን ወደ አዲስ የዕድገትና የብልፅግና ምዕራፍ ያሸጋገረ ሀገራዊ ስኬት ነው።
እነዚህ ግዙፍ የልማት ሥራዎች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ጂኦፖለቲካዊ የማስፈጸም አቅም በተግባር ያረጋገጡ ከመሆናቸውም በላይ የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ የለወጡ ናቸው።
የዚህ ታላቅ የልማት ጉዞ ዋነኛ ማረጋገጫና የኢትዮጵያውያን ኩራት የሆነውና ለዓመታት ሲጠበቅ የነበረው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ በሙሉ አቅሙ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ነው።
ግድቡ ለሀገር ውስጥና ለጎረቤት ሀገራት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከመስጠቱ ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በራሷ የፋይናንስና የቴክኒካዊ አቅም ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ዳር ማድረስ እንደምትችል ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተግባር ያሳየ ታሪካዊ ክስተት ነው።
በተመሳሳይ መልኩ፣ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑት የወንዝ ዳርቻ ልማትና የከተሞች ኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች የከተሞችን ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመቀየር ለነዋሪዎች ምቹና ዘመናዊ ካባቢዎችን ፈጥረዋል።
ዘመናዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ የእግር መንገድ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የብስክሌት መስመሮችና የአረንጓዴ ስፍራዎች ልማት የከተሞችን ውበት፣ የቱሪዝም መስህብነትና የንግድ እንቅስቃሴ በጥራት አሳድገውታል።
ከእነዚህ ከተከናወኑት ልማቶች በተጨማሪ፣ ግዙፉ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የጎዴ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የታዳሽና የኒውክሌር ኃይል አማራጮች እንዲሁም የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን የወደፊት የኢኮኖሚ መዋቅር በጽኑ መሠረት ላይ የሚጥሉ ናቸው።
እነዚህ የታቀዱና በሂደት ላይ ያሉ ጥረቶች የውጭ ምንዛሪን ከመቆጠብ ባለፈ ኢትዮጵያን በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የንግድ፣ የኃይልና የሎጅስቲክስ ማዕከል ያደርጓታል።
እነዚህን ግዙፍ ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ለማከናወን ያስቻለው ዋነኛ ምስጢር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር) ቁርጠኛ አመራር፣ የውስጥ ሀብትንና የዳያስፖራውን አስተዋጽዖ ማስተባበር መቻሉ እንዲሁም የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነትን መጠቀም ነው።
በተጨማሪም በጠንካራ የሥራ ክትትልና በቅርብ ቁጥጥር ፕሮጀክቶችን በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት አጠናቆ የማስረከብ አዲስ የሥራ ባህል መገንባት ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል።
በአጠቃላይ፣ የመደመር መንግሥት ያስመዘገባቸው ታላላቅ የልማት ስኬቶች ኢትዮጵያ "አይቻልም" የሚለውን አስተሳሰብ ሰብራ በራሷ አቅም የታለሙ ግቦችን ማሳካት እንደምትችል ማረጋገጫ ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የሚያጠናክሩ፣ ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩና ለቀጣዩ ትውልድ ጽኑ፣ የተከበረችና የበለጸገች ኢትዮጵያን የሚያስረክቡ ታሪካዊ መሠረቶች ናቸው።
በአብረሃም አበራ

24 days ago