Logo
Getu Temesgen
የሃላንድ ጎል መሰረዝ ነበረበት ሲል ፕሮፌሽናል ሬፍሪ አረጋገጠ
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የማንቸስተር ዩናይትድና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ በ60ኛው ደቂቃ የኤርሊንግ ሃላንድ ያስቆጠረው ጎል በትክክል መሰረዝ ነበረበት ተባለ።

የፕሮ ሬፍስ ባለሥልጣናት እንዳብራሩት፣ በሜዳ ላይ መጀመሪያ የተሰጠው ውሳኔ ሃላንድ ኦፍሳይድ ነው የሚል ነበር። ሆኖም ጉዳዩ በVAR ሲመረመር ሃላንድ ኦንሳይድ ላይ እንደነበር ተወስኗል።

ነገር ግን በዚያው ጥቃት ወቅት ኤንዞ ፈርናንዴዝ ኳሱን እንዳልነካ ተረጋግጧል። በዚህም የኦፍሳይድ ጥሰቱ የፈረንሳይ ወይም የእንግሊዝ ቋንቋ እንደሚሉት subjective ውሳኔ የሚፈልግ ሆኗል።

ፕሮ ሬፍ እንደገለጸው፣ VAR የፈርናንዴዝ አቀማመጥ በጨዋታው ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽዕኖ በበቂ ሁኔታ ሳያስተውል ቀርቷል። በመሆኑም VAR ዳኛው ወደ ሜዳ ተመልሶ ሁኔታውን እንዲመለከት ማሳሰብ ነበረበት ብሏል።

ፕሮ ሬፍ በተጨማሪም ለማንቸስተር ዩናይትድ ጉዳዩን እንደ “የፍርድ ስህተት” በመቀበል ይቅርታ/ማብራሪያ መስጠቱን ገልጿል። በክስተቱም ላይ ተጨማሪ ግምገማ እንደሚደረግ አስታውቋል።

የጨዋታው ውሳኔ በVAR ላይ አዲስ ክርክር አስነስቷል!

24 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.