አትሌት ልቅና አምባው የ5 ሺህ ሜትር የአልቲሜት ሻምፒዮና አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአልቲሜት ሻምፒዮና የመጨረሻ ቀን በተካሄደው የሴቶች 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ልቅና አምባው ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቅ የሻምፒዮናው አሸናፊ ሆናለች።
አትሌቷ ርቀቱን 14 ደቂቃ፣ 30 ሰከንድ፣ 36 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ ችላለች።
ሌላኛው አትሌት ፋንታዬ በላይነህ 3ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፋለች።
አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ 4ኛ፣ አትሌት አለሺኝ ባወቀ 5ኛ እንዲሁም አትሌት ሰናይት ጌታቸው 7ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
አውስትራሊያዊቷ አትሌት ጄሲካ ሂል በሁለተኛነት ውድድሯን አጠናቃለች።

25 days ago