Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሚመራው የሩሲያ ከፍተኛ ልዑክ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር የሁለትዮሽ የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ውይይት አካሂዷል። በዚህ ወሳኝ መድረክ ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ እና አስተማማኝ አጋር ሲሉ ያሞገሷት ሲሆን፣ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በእኩልነት እና በጋራ ተጠቃሚነት መርሆዎች ላይ ተመሥርቶ እያደገ መምጣቱን አስገንዝበዋል።

በተለይም በኢኮኖሚው ዘርፍ ያለውን የጎላ መሻሻል በተመለከተ ፕሬዝዳንት ፑቲን በሰጡት ማብራሪያ፣ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጣችን ጠንካራ መሠረት ይዟል፤ የንግድ መጠናችን ከሦስት እጥፍ በላይ ያደገ ሲሆን አሁንም በቀጣይነት በማደግ ላይ ይገኛል፤ ይህም እጅግ በጎ ማሳያ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በመጪው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን በሞስኮ ለማስተናገድ በጉጉት እንደሚጠብቁ አክለው ገልጸዋል።

ይህ የፕሬዝዳንት ፑቲን አዎንታዊ ንግግር ሩሲያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ ተጽዕኖ ይበልጥ ለማጠናከር እና ከምዕራባውያን ጫና ውጭ የሆኑ ጠንካራ የንግድ አጋሮችን ለማፍራት የምታደርገውን የዲፕሎማሲ ጥረት በግልጽ የሚያሳይ ነው። የንግድ ልውውጡ ከሦስት እጥፍ በላይ ማደጉም፣ ኢትዮጵያ በቅርቡ ከተቀላቀለችው የብሪክስ ስብስብ እና ከሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር አንጻር እያገኘች ያለውን የገበያ አማራጭ ያመለክታል። ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሞስኮው ጉባኤ ላይ ለማየት ጓጉቻለሁ ማለታቸው፣ ሞስኮ አዲስ አበባን በአፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ እንደ ቁልፍ መግቢያ በር እያየቻት መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

ለኢትዮጵያ ማን ይሻላታል?
1. ሩሲያ
2. አሜሪካ
3. ዥዋዥዌ

26 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.