Logo
Getu Temesgen

የኢትዮጵያ ተወካይ ወጣቶች በዓለም አቀፉ የወጣቶች ፌስቲቫል ለመሳተፍ ሩሲያ ገቡ
#ethiopia | በሩሲያዋ የካቲሪንበርግ ከተማ ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው የ2026 ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ ተወካዮች ቦታው ደርሰዋል።

በዚህ ታላቅ መድረክ ከ196 አገራት የተወጣጡ 10 ሺህ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች እና 10 ሺህ የሩሲያ ወጣቶችን ጨምሮ በድምሩ 20 ሺህ ታዳሚዎች ይገኛሉ።

በተጨማሪም የልዩ ልዩ አገራት መሪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ የቴክኖሎጂ ባለቤቶች፣ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት ተወካዮች እና ከያኒያን ይታደማሉ።

ኢትዮጵያን ወክለው ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተመረጡት እነዚህ ወጣቶች በዝግጅቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሲሆን፣ በተለይም የኢትዮጵያን ቡና እና የተለያዩ ባህላዊ ሀብቶቻችንን የማስተዋወቅ ሥራ ያከናውናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#russia #youthfestival #ethiopiancoffee #culture #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.