አኮያ ፕሮፐርቲስ የ2026 የዲሲ እና ቶሮንቶ ዲያስፖራ ኤክስፖ ዋና ስፖንሰር ሆነ
በግንባታ ጥራት፣ በዘመናዊ ዲዛይንና በደንበኛ ተኮር አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ የሚገኘው አኮያ ፕሮፐርቲስ (AKOYA Properties)፣ "ኢትዮ ቱ አሜሪካ" በተሰኘው ድርጅት አዘጋጅነት በሚካሄደው የ2026 የዲሲ እና ቶሮንቶ ዲያስፖራ ኤክስፖ (2026 DC & Toronto Diaspora Expo) ዋና (የፕላቲኒየም) ስፖንሰር ሆኖ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
የአጋርነቱ ይፋዊ የፊርማ ስነ ስርዓት ረቡዕ ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በአኮያ ፕሮፐርቲስ ዋና መስሪያ ቤት የተካሄደ ሲሆን፣ በዕለቱም የአኮያ ፕሮፐርቲስ ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራ አመራሮች፣ የኤክስፖው አዘጋጅ "ኢትዮ ቱ አሜሪካ" ተወካዮች፣ የኤክስፖው ብራንድ አምባሳደር ቲክቶከር አዶናይ ብርሃነ፣ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሚዲያ አካላት ተግኝተዋል።
ይህ አጋርነት አኮያ ፕሮፐርቲስ የሪል እስቴት ፕሮጀክቶቹን በውጭ አገር ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማሕበረሰብ አባላት በስፋት የሚያስተዋውቅበትን ትልቅ መድረክ የሚፈጥርለት ሲሆን፣ የዲያስፖራ ካፒታልንና የኢንቨስትመንት ፍላጎትን ከአገር ውስጥ የንግድ አጋርነት ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ነው።
በተጨማሪም በአገር ውስጥ ላሉ ደንበኞች ከመስከረም 5 እስከ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ ፊት ለፊት፣ ራማዳ ሆቴል አቅራቢያ በሚገኘው ናይል ሶርስ ሕንጻ 8ኛ ፎቅ (በድርጅቱ ዋና ቢሮ) ልዩ የቤት ሽያጭ ኤክስፖ እና የልዩ ቅናሽ አማራጮች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
አኮያ ፕሮፐርቲስ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር ባደረገው የትብብር ስምምነት መሰረት፣ ለመኖሪያ ቤት እና ለንግድ ሱቅ ገዢዎች (በተለይም ለዲያስፖራ ደንበኞች) የተመቻቸ ልዩ የወለድ ነጻ የተራዘመ የክፍያ አማራጭ አቅርቧል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የወለድ ነጻ ባንኪንግ አገልግሎት ዋና ሃላፊ አቶ ርዕስቱ ከማል እንደገለጹት፤ የዲያስፖራ ደንበኞች የንብረቱን ዋጋ 15 በመቶ ብቻ እንደቅድመ ክፍያ በመክፈል፣ ቀሪውን 85 በመቶ በባንኩ በኩል በተራዘመ የክፍያ ሁኔታ እንዲከፍሉ የሚያስችል ልዩ የፋይናንስ አማራጭ ተመቻችቷል። ይህ አሰራር ደንበኞች የሚፈልጉትን የመኖሪያ ቤት ወይም የንግድ ሱቅ በቀላልና ተመጣጣኝ ሁኔታ እንዲገዙ የሚያስችል ነው።
አኮያ በንግዱ ዓለም የ14 ዓመታት፣ በሪል እስቴት ዘርፍ ደግሞ የ5 ዓመታት ልምድ ያለው፣ በአዲስ አበባ የተመሰረተ ግዙፍ ኩባንያ ነው። “ጥራት፣ ዘመናዊ ዲዛይን እና ዘላቂ እሴት” የሚለውን መርሕ በማንገብ እስከ አሁን 3 ፕሮጀክቶችን በጥራት ገንብቶ ለደንበኞች ያስረከበ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2025 የኢትዮ ሪል እስቴት የአርክቴክቸር ልቀት ሽልማትን ማሸነፉ ይታወሳል።
ኩባንያው ከሪል እስቴት ዘርፍ ባሻገር በእሕት ኩባንያዎቹ አኮያ ሞተርስ፣ አኮያ ኮፊ (AKOYA Coffee) እና ኢንያዝ ኮንስትራክሽን (INYAZ Construction) በንግድና ግንባታ ዘርፎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። እንዲሁም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በሪል እስቴት ዘርፍ የመጀመሪያው የሼባ ማይልስ ፕላቲኒየም አጋር ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል።

28 days ago