"የባህር በር ማግኘት ጉዳይ በሰላም ካልሆነ በጉልበትም ቢሆን አይቀርም" ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ"‼️
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የባህር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ የንግድ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ደህንነት እና የህልውና ማስከበሪያ እንደሆነ ገልጸዋል።
• ጥያቄው በሰላማዊና በሁለቱም ወገን አሸናፊነት (Win-Win) መንገድ እንዲፈታ ቅድሚያ የሚሰጥ ቢሆንም፣ በሰላም ካልሆነ ግን ሀገሪቱ በጉልበትም ቢሆን ፍላጎቷን አሳልፋ እንደማትሰጥ አስጠንቅቀዋል።
• ኢትዮጵያ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት የባህር በር እንደነበራት ያነሱት ፕሮፌሰሩ፤ ባለፉት 50 ዓመታት በነበሩ የፖለቲካ ችግሮች እና በህወሓት የስልጣን ፍላጎት ምክንያት ጥያቄው ውይይት ሳይደረግበት መታለፉ ትልቅ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን ጠቁመዋል።
• ግብፅ አባይን የህልውናዋ ጉዳይ እንደምታደርገው ሁሉ፣ ለ130 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብም ቀይ ባህር የህልውና ጉዳይ መሆኑን እና ከውጭ ስጋት ራስን ለመከላከል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
• የኃያላን ሀገራት የመራኮቻ ቀጠና እንዳይሆን፣ በቀይ ባህር አካባቢ ያሉ ጎረቤት ሀገራት ከውጭ ሀገራት ተፅዕኖ ወጥተው ለጋራ ጥቅም እና ደህንነት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ መስራት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
Seledadotio

28 days ago